2010-02-22 14:08:41

የክህነት ጥሪ እንዲበራከት


ባለፈው ዓርብ እዚህ ሮማ በሚገኘው ባዚሊካ ዘቅዱስ መስቀል ዘኢየሩሳሌም ለክህነት ጥሪ መበራከት እግዚአብሔር ልኡካን እንዲያበዛ የሮማ ከተማ ሰበካ የህነት ዓመት ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው RealAudioMP3 የጸሎት መርሃ ግብር መከናወኑ ተገለጠ።

የቤተሰብ ፍቅር የተሰኘው የቤተ ክርስትያን እንቅስቃሴ ረዳት አባ ስቴፋኖ ታርዳኒ ስለ ተካሄደው የጸሎት ሥነ ሥርዓት በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የጸሎት ሥነ ሥርዓት የክህነት ጥሪ እንዲበረክት ብቻ ሳይሆን በውሉደ ክህነት እና በአለማውያን ምእመናን መካከል ያለው ግኑኝነት እና ትብብር እንዲጎለበት ጭምር ዓልሞ የተከናወነ መሆኑ በመጥቀስ፣ ካህን ከክርስቶስ ጋር ያለው ጥብቅ ወዳጅነት ያጎላ ሕይወት በመኖር የዚህ ፍቅር አብነት እንዲሆን የተነቃቃበት መርሃ ግብር እንደነበር አስታውሰው፣ የክህነት ጥሪ እንዲበራከት የዚህ እቅድ ቅድሚያ ተወናያን ክርስትያን ቤተሰብ መሆኑም ገልጠው፣ ለክህነት ጥሪ ክርስትያን ቤተሰብ መሠረት ነው ብለዋል።

በዚህ በተካሄደው የጸሎት ሥነ ሥርዓት ካህናት የሚያስፈልጋቸው ሰብአዊ እና ባህላዊ ፍልስፍናው እና ቲዮሎጊያዊ ህንጸት ባሻገር የሕዝብ ድጋፍ እና ትብብር እንደሚያስፈልጋቸውም ያሳሰበ እና ቀጥሎም እያንዳንዱ ካህን ባለው የክህነት ጥሪ መሠረት አንድነት እና ውህደት ያለው እንዲሆን የሚል ሲሆን፣ በሶስተኛ ደረጃም በካህናት መካከል ያለው ትብብር በማጠናከር ከዓለማውያን ምእመናን ጋር ያለው ተባብሮ የእግዚአብሔር መንግሥት ማስፋፋት ላይ ያተኮረ የጸሎት መርሃ ግብር እንደነበር አብራርተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.