2010-02-22 14:07:16

የክህነት ዓመት፣ የምስክርነት ዓምድ


በዚህ ዘንድሮ በመታሰብ ላይ ያለው የክህነት ዓመት ምክንያት በአደንዛዥ እጽዋት ተገዥ የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍል ከወደቁበት አደገኛው ሕይወት ይላቀቁ ዘንድ መንፈሳዊ እና ስነ አዕምሮአዊ ድጋፍ በመስጠት አገልግሎት RealAudioMP3 የተጠመዱት አባ ጆርጆ ቦሲኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የሚሰጡት አገልግሎት ማዳመጥን እና እግዚአብሔር እንደሚያፈቅረን በሚያረጋገጥ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ላይ የተመሠረተ መሆኑ በመግለጥ፣ በዚህ 30 ዓመት ባስቆጠረው ማኅበራዊ እና ሰብአዊ በተለይ ደግሞ ቤተ ክርስትያናዊ ተልእኮአቸው ወጣቱን ትውልድ በእምነት ታድሶ የእግዚአብሔር ፍቅር የሕይወቱ ማእከል በማድረግ ከወደቀበት አደገኛው የአደንዛዥ እጽዋት ባርነት ይላቀቅ ዘንድ በመደገፍ ላይ እንደሚገኙ ገልጠዋል።

የአደንዛዥ እጽዋት ተገዥ መሆኑ ወጣቱ ያለበት ለተወሳሰበው ችግር ምልክት ነው። ስለዚህ ወጣቱ የአደንዛዥ እጽዋት ተገዥ እንዲሆን የሚገፋፋው ምክንያት በመለየት ከወደቀበት ክብር ሰራዥ እና የሞት ባህል እንዲላቀቅ ማነጽ የሚለው እቅድ እ.ኤ.አ. በ 1970 ዓመታት የተነቃቃ ዓላማ መሆኑ ዘክረው፣ በዚህ አለማ ከተለያዩ የቤተ ክርስትያን የበጎ አድራጎት አባላታ ወጣቶች ጋር በመሆን የእግዚአብሔር ፍቅር ማእከል ያደረገ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እያከናወኑ መሆናቸው ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.