2010-02-22 14:04:44

ክርስትያን የፖለቲካ አካላት


ባለፈው ዓርብ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ በኢጣልየር ሪቾነ ከተማ የኢጣሊያ የፖሊቲካ አካላት ማኅበር አቀነባባሪ ኮሜተ ባካሄደው ዓመታዊ ስብሰባው ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ አዲስ RealAudioMP3 ክርስትያን ትውልድ የፖለቲካ አካላት እጅግ አስፈላጊ ናቸው። እነዚህ ክርስትያን የፖለቲካ አካላት ልዑል ወደ ሆነው የሕይወት ክብር እና እሰይታ ያተኩረ ማኅበርሰብ እንዲጸና በቃል እና በሕይወት የሚያስተምሩ በማኅበራዊው ጉዳይ አብነት ሆነው የሚያገለግሉ መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ሰብአዊ ክብር፣ ድጋፍ እና ትብብር መሠረት ያለው ብሔራዊ ጥቅም መረጋገጥ ይኖርበታል ይህ ደግሞ የአገር እና የሕዝብ ጥቅም ማስቀደም ማለት መሆኑ በማብራራት፣ የላቀውን እሰይታ ማእከል ያደረገ ሥርዓት ማነቃቃት ማለት ነው ብለዋል። ብዙዎን ጊዜ ፖለቲካ ቆሻሻ ነው የሚባለው አነጋገር መሠረት የሌለው ባዶ አባባል መሆኑ በማስረዳት፣ ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ አስራ አንደኛ ፖለቲካ መልካም ፖለቲካ የሚሆኖነው የባለንጀራ ፍቅር መግለጫ ሲሆን ነው በማለት የሰጡት ፍች በማስታወስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በፖለቲካ ዓለም ማገልገል ጥሪ እና ለማኅበራዊ ድህነት ማገልገል ማለት ነው ያሉትን አስተጋብተዋል።

ቶማስ ሞር ፖሊቲካ አገልግሎት ነው በማለት ይገልጠዋል። ማኪያቨሊ ፖሊቲካ ጥበብ እና በሚስጠው ጥቅም አንጻር የገመገማል በማለት የሰጠው ማብራሪያ በማስታወስ፣ የቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ ትምህርት ላይ በማተኮር ሰውን ማእከል ያደረገ ተጨባጩን የሰው እና የዓለም ሕይወት ግምት የሚሰጥ የፖለቲካዊ ሥርዓት መረጋገጥ ይኖርበታል፣ የቤተ ርክስትያን ማኅበራዊ ትምህርት ኵላዊነት ለበስ መሆኑ በስፋት ካስረዱ በኋላ፣ ፖለቲካ ሊተገበር የማይቻለው ባዶ ተስፋ የሚነዛበት መድረክ መሆን የለበትም ስለዚህ ለቅድስና ያተኮረ ፖለቲካ ወሳኝ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.