2010-02-22 14:06:01

ቅዱስ አንጦኒዮስ ዘ ፓዶቫ


የቅዱስ አንጦኒዮስ ቅዱስ አጽም እና ትሩፋት እ.ኤ.አ. በ 1981 ዓ.ም. 750ኛው ዝክረ እረፍት ምክንያት ለህዝብ መቅረቡ የሚዘከር ሲሆን፣ ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ልክ ከ 29 ዓመት በኋላ ከውስጥ እና ከውጭ አገር RealAudioMP3 ለሚመጡት መእመናን ነጋድያን መቅረቡም ይታወሳል።

የቅዱስ አንቶኒዮስ ዘ ፓዶቫ አጽም የሚቀመጥበት በቅዱስ አንጦኒዮስ ባዚሊካ በሚገኘው ጸሎት ቤት እንድሳት ተጠናቆ ወደ ሥፍራው መመለሱ ሲገለጥ፣ የቅዱስ አንጦኒዮስ ዘ ፓዶቫ ቅዱስ አጽም እና ትሩፋት ለመጎብኘት የጎረፈው የሕዝብ ብዛት እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ሜሳጀሮ ዲ ሳንታአ’ቶኒዮ የተሰየመው መጽሔት ዋና አዘጋጅ ኣባ ኡጎ ሳርቶሪዮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ጠቅሰዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቅዱስ አንጦኒዮስ ዘ ፓዶቫ አቢይ ታዋቂነት ካላቸው የቤተ ክርስትያን ቅዱሳት ውስጥ አንዱ መሆኑ ገልጠው እንደነበር የሚዘከር ሲሆን፣ ቅዳሜ የቅዱስ አንጦኒዮስ ቅዱስ አጽም እና ርቱፋት ለነጋድያን ምእመን የቀረበበት ዕለት መዝጊያ ምክንያት የቴሌግራም መልእክት አስተላልፈዋል። በትላትናው ቅዳሜ 60 ሺሕ ምእመናን የቅድስ አንጦኒዮስ አጽም ለመሳለም መገኘታቸውም ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት የቴሌግራም መልእክት፣ ቅዱስ አንጦኒዮስ በእያንዳንዱ ነጋድያን ምእመን ለክርስቶስ እና ለባለጀራው ያለው ፍቅር ያነቃቃ ዘንድ እና ሁሉም እምነቱን አድሶ ለወንጌል እና ለቤተ ክርስትያን ያለው ፍቅር እንዲኖር አደራ በማለት፣ ቅዱሳት ወንጌላዊ ሕይወት የሚቻል መሆኑ የሚያረጋገጡልን የእምነት አብነት ናቸው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.