2010-02-19 14:56:03

የባህሎች መቀራረብ ዓመት


የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፡ የስነ ጥበባትና የባህል ድርጅት እ.ኤ.አ. ከ 2001 እስከ 2010 ዓ.ም. የሰላም ባህል ለማነጽ እንዲቻል በሚል የላቀ ዓለማ የወጠነው እቅድ መሠረት ዘንድሮ በባህሎች መካከል ያለው መቀራረብ RealAudioMP3 መተዋወቅ የሚጎለብትበት ዓመት እንዲሆን ከፓሪስ ከሚገኘው ዋናው ጽ/ቤት አስታውቀዋል።

መተዋወቅ፣ ለጋራው መግባባት መሠረት መሆኑ የዩኒስኮ መግለጫ በማመልከት፣ መግባባት በአገሮች መካከል ስምምነት እንደሚያረጋገጥ ይህ ድርጅት የ 60 ዓመታት ገጠመኙን መሠረት በማድረግ በመጥቀስ ይኽንን የባህሎች መቀራረብ የሚያነቃቃ የተለያዩ የባህል የትርኢት የአውደ ጥናት መርሃ ግብሮች መወጠኑ ለማወቅ ተችለዋል።

ባህል ስነ ጽሕፍ ስነ ጥበብ ብቻ ማለት ሳይሆን፣ የአኗኗር ዘይቤን የአንድ ማኅበረሰብ የትሥሥሩ መሠረት ውህደት እሴቶች እምነቶችን ጭምር የሚያጠቃልል ማለት መሆኑ የዩኔስኮ መገልጫ በማብራራት፣ የሚለያየውን አቢይ ግምት በመስጠት አንድ ካንዱ የሚለየውን አውቆ ልዩነቱ ሃብት መሆን ተረድቶ የተዋሃደ ኅብረትሰብ ለማነቃቃት የሚደግፍ ዓመት መሆኑ መግለጫው ያመለክታል።

ስለዚህ በአለማችን ያለው ግጭት አለ መግባባት ባህሎችን በማወያየት እና በማቀራረብ ዘላቂ መፍትሔ ሊያገኝ እንደሚችል የማይታበል ሓቅ መሆኑ የዩኔስኮ ዋና አስተዳዳሪ ኢሪና ቦኮቫ በማብራራት ይኸንን የሚያነቃቃ አንድ የሰላም እና የውይይት ቡድን መመልመላቸው አስታውቀዋል።

ይህ የተመለመለው ቡድን በባህሎች መካከል ውይይት፣ ላንድ አዲስ የሰላም መንገድ በሚል ርእስ ሥር የባህሎች መቀራረብ ሂደት የሚያነቃቃ የክብ ጠረጴዛ ውይይት መጥራቱንም ተረጋገጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.