2010-02-19 14:54:46

አልጀሪያ፣ የሃይማኖት ነጻነት


ባለፈው ሳምንት በአልጀሪያ ርእሰ ከተማ የሃይማኖት ነጻነት በሚል ርእስ ሥር የሃይማኖት መሪዎች RealAudioMP3 እና የፖለቲካ አካላት የተሳተፉበት ዓውደ ጥናት መካሄዱ ተገለጠ።

ከተካሄደው አውደ ጥናት ለመረዳት እንደተቻለውም በዚህች አገር የሃይማኖት ነጻነት ውሱን እየሆነ መምጣቱ ለመረዳት ተችለዋል።

እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. በአልጀሪያ ምስልምና ያልሆኑ ሃይማኖቶች በይፋ በሚሰጣቸው ክልል እና የጸሎት ቤት የተወሰነ የእምነት እና የሃይማኖት ሥርዓት መፈጸም ይኖርባቸው የሚል የጸደቀው የትእዛዝ ሕግ፣ መሠረት ከምስልምና ሃይማኖት በስተቀረ ሌሎች ሃይማኖቶች ይኽንን ሕግ ሊያከብሩት እንደሚገባቸው በይፋ የተገለጠ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. አንድ ፈረንሳዊ ካህን ከድቡባዊ ሰሃራ የመጡት ክርስትያን ስደተኞች ጋር በመሆን የጸሎት ሥነ ሥርዓት እያከናወኑ እያሉ፣ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ከተሰጠው ይፋዊ ጸሎት ቤት ውጭ የሃይማኖት ሥነ ሥርዓት ፈጽመዋል በሚል ክስ ለእስር መዳረጋቸውም የተካሄደው አውደ ጥናት እንደ አብነት በመግለጥ፣ የሃይማኖት ነጻነት በአደጋ ላይ መሆኑ አስምሮበታል።

በአልጀሪያ የክርስትያን ማኅበርሰብ ብዛት አንድ በመቶ ሲሆን የምስልምናው ሃይማኖት ተከታይ 99 በመቶው መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ በአገሪቱ እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. የጸደቀው ሕግ የክርስትያኖች ነጻነት ምን ያክል ይወስናል ለሚለው ጥያቄ የአልጀሪ ሊቅ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጋለብ ባደር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሂዱት ቃለ ምልልስ ሲያብራሩ፦ ሕጉ ክርስትያኖች ልኡካነ ወንጌል የሚሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት በቤተ ክርስትያን እና በጸሎት ቤቶች ውስጥ እንዲታጠር የሚያስገድድ፣ ሌሎች አቢያተ ክርስትያን ለመገንባት እንቅፋት ወይንም ፈቃድ ለማግኘት የሚደረገው አሠራር እጅግ እንዲወሳሰብ የሚያደርግ ነው። ሕጉ ባንድ በኩል የሃይማኖት ነጻነት የሚፈቅድ በሌላው ረገድ የሚወስንም ነው። ስለዚህ ሕጉ አሻሚ እና ግራ የሚያጋባ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.