2010-02-19 14:53:30

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከሮማ ሰበካ ካህናት ጋር ተገናኙ


ትላትና ቫቲካን በሚገኘው የቡራኬ የጉባኤ አዳራሽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከሮማ ሰበካ ካህናት ጋር በመገናኘት ክህነት እና ካህን ምን ማለት መሆኑ ሰፊ እና ጥልቅ ትምህርት RealAudioMP3 መስጠታቸው ተረጋገጠ።

የሮማ ካህናት በሮማ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ ተሸኝተው ከቅዱስ አባታችን የእብራውያን መልእክት መሠረት ያለው ንባበ መለኮት ማዳመጣቸው ሲገለጥ፣ ካህን ሰው እና ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር ሰው የሌላውን ስቃይ ችግር ተካፋይ በመሆን እንዲሁም ለእግዚአብሔር ታዛዥ በመሆን መንፈስ ተገፋፍቶ ሁሉምንም በፍቃዱ በመተው፣ በነጻነት እግዚአብሔርን የሚከተል መሆኑ የሚያስረዳን ቅዱስ አባታችን ያቀረቡት ትምህርተ መለኮታዊ ንባብ በመቀጠልን መሲህነት በቡሉይ ኪዳን ያለው አገላለጥ በመተንተን፣ ክርስቶስ በማዳን እቅድ ያለውን ማእከልነት እስረድተዋል። በብሉይ ኪዳን መሲሕ ንግሥና የሚለብስ እግዚአብሔር የመረጠው ማለት መሆኑ ገልጠው፣ ወደ እብራውያን በተጻፈው መልእክት ዘንድ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 110 “በመልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘለዓለም ካህን ትሆናለህ” የሚለውን ቃል በመጥቀስ ካህን ማህላው የማይሻር መሆኑ በዚህ መዝሙረ ዳዊት በሚገባ በአዲስ ብርሃን ተገልጦ እንደሚገኝ ገልጠዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ የዳዊታዊው ቃል ፍጻሜ ሳይሆን እውነተኛው የእስራኤል፣ የዓለም ንጉሥ እና የእውነተኛ ቃል ካህን ነው። በክርስቶስ ዘንድ ሁለት ቃል ኪዳኖች ተዋህደው እናገኛለን ይህ ደግሞ ክርስቶስ እውነተኛው ንጉሥ እና እውነተኛው የእግዚአብሔር ልጅ እንዲሁም እውነተኛው ካህን ነው። ፍጹም መሥዋዕት የሚያቀርብ የተሰዋ እውነተኛው ካህን በክርስቶስ ተገልጧል። እርሱ እውነተኛ የተገባ መሥዋዕታችን ነው። ስለዚህ ካህን ምን ማለት መሆኑ በክርስቶስ ተገልጦልናል በርሱም ዘንድ በሙላት ተረጋገጠዋል ብለዋል።

የክርስቶስ ክህንነት መሠረት የክህነት ጥሪ ትርጉም ካስረዱ በኋላ፣ አንድ ካህን እግዚአብሔርን እና ሕዝብን የሚያገናኝ ድልድይ ለመሆን፣ በቅድሚያ ሰብአዊነቱን መልበስ፣ እግዚአብሔር ሥጋችን ለብሶ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የክህነት እውነተኛው ትርጉም ጠልቆ መረዳት። ሰዎችን እና መለኮታዊን የሚያገናኝ ጸላይ እና ቅዱስ ቁርባን ዕለት በዕለት ካለ ማቋረጥ የሚመገብ መሆን አለበት። በክርስቶስ ሚሥጢር ለመካፈል ብቃትቱን የሚስጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው፣ ካህን በራሱ ኃይል እና ብቃት ሊሰጠው የማይችለውን የላቀውን እና ፍጹም ስጦታ ለመስጠት የተጠራ፣ ስለዚህ ይኽ ስጦታ ከእግዚአብሔር ተቀብሎ የእግዚአብሔር ሰው በመሆን እግዚአብሔርን የሚያውቅ፣ የእግዚአብሔርን እና የክርስቶስን አንድነት የሚኖር በውህደቱ የሚተባበር መሆን እዳለበት ገልጠዋል።

ካህን ለመሆን የተጠራ፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሰብአዊ ስሜቱን በትክክል የሚኖር፣ ይኸንን ስሜት የሚያጎለብት ዕለት በዕለት የሚለወጥ፣ ኃሰት መናገር እና ቅጥፈት ሰውብአዊ ነው የሚለው አነጋገር የማይቀበል፣ የፍትሕ እና የእውነት ሰው በመሆን፣ ቸር ትሁት በክርስቶስ ድጋፍ መሠረት ሰብአዊነቱን ቅጥ የሚያስይዝ መሆን ይገባዋል ብለዋል።

በዓለም የሚኖር የዓለም ያልሆነ ዓለም እና ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ያቀና ዘንድ ከክርስቶስ ጋር በክርስቶስ እና ከክርስቶስ ጽኑ አንድነት በመመሥረት የመሚመራ የጥሪ ኃላፊነት ያለው ነው።

ተአዝዞ ማለት ባርያ መሆን በሌላ ውሳኔ መመራት እራስን መተካት ማለት አይደለም፣ ስለዚህ ተአዝዞ በሌላ አነጋገር ነጻነት ማለት መሆኑ ገልጠው፣ የእግዚአብሔር ፍቃድ የጨቋኝ ፈቃድ ሳይሆን እውነተኛው መለያችን እና ማንነታችን የምናገኝበት ሥፍራ ነው ካሉ በኋላ፣ ስለዚህ የዚህ ፈቃድ ታዛዥ መሆን ሰብአዊው ድክመታችን የሚደክምበት ሥፍራም መሆኑ አብራርተው፣ በቃል እና በሕይወት በትኅትና በጸሎት እና ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት በመፍጠር ነጻነት እና ተአዝዞ በደስታ በመኖር ህዝብን ወደ እግዚአብሔር ለመምራት እንድንችል እንጸልይ በማለት ያሰሙት መለኮታዊ ንባብ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.