2010-02-17 14:19:02

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርጠለሚዮስ መልእክት


በላቲን ሥርዓት ለተገባው አቢይ ጾም ምክንያት፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርጠለሚዮስ አንደኛ መልእክት ማስተላለፋቸው ሲገለጥ፣ ጾም መንፈስን ሕይወትን ከተለያዩ መጥፎ ልማዶች ተግባሮች ለማንጻት እና ሥጋችን RealAudioMP3 ከአጉል አሳሳች ልቅ ለጥፋት ከሚወስደው መንገድ ነጻ ለማድረግ የምንገለገልበት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ መሆኑ ማብራራታቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ጾም፣ ይበቃኛል ማለት፣ በተስተካከለ ሕይወት መኖር ፍላጎትን እና ስሜትን ሚዛኑን የሚያስጠብቅ በተጠራህበት ጥሪ እንዲኖር የሚያደርግ ጸጋ መሆኑ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለሚዮስ አንደኛ ባስተላለፉት መልእክት በማብራራት፣ እላፊውን፣ ትርፈ ትርፉን በማግለል በልክ መኖር የምንማርበት አቢይ ወቅት ነው ካሉ በኋላ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የሚወርድብን የፍጆት ማስታወቂያ ተገዥ እንዳንሆን በተመጣጠነው ሕይወት እንድንኖር የሚደገፍን የሚያነቃቃን የሚያበረታታን ወቅት ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.