2010-02-17 15:29:14

የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ረቡዓዊ አስተምህሮ


ውድ ወንድሞቼ እና እኅቶቼ

ዛሬ የአርባ ጾም ጉዞ የአመድ ሮብ በማክበር እንጀምራለ። የተጀመረው የአቢይ ጾም ጉዞ ለ 40 ቀናት የሚቆይ ሆኖ ወደ ትንሣኤ ክርስቶስ ወደ ሆነው በዓለ ፋሲካ ያደርሰናል።

በዚሁ መንፈሳዊ ጉዞ ቤተ ክርስያን ከመጀርያውኑ በእግዚአብሔር ቃል ስለምትደግፈን እንዲሁም በምናደርገው ብርቱ የንስሓ ጥረት በቅዱሳት ሚሥጢራት ጸጋ ስለምትረዳን መንፈሳዊ ሂደቱ ስናጠቃልል ብቻችን አይደለንም።

አሁን የሰማነው የሐዋርያ ጳውሎስ ቃላት ልንከተለው የሚገባንን መንገድ በትክክል ያመለክቱናል። “የተቀበላችሁት ጸጋ በከንቱ አታስቀሩት ብለን እንለምናችኋለን… እነሆ የተመረጠው ሰዓት አሁን ነው የደኅንነትም ቀን አሁን ነው” በእውነቱ በክርስትያን ሕይወት እያንዳንዱ ጊዜ የተመረጠ ሰዓት፣ እያንዳንዱ ቀንም የድኅነት ቀን መሆን አለበት።”

የቤተ ክርስትያን ሥርዓተ አምልኮ እነዚህን ቃላት ለየት ባለ መንገድና ጊዜ በአቢይ ጾም ጊዜ ይጠቀምባቸዋል። እነኚህ የአርባ ጾም አርባ ቀናት የተመረጡ ጊዜያትና የጸጋ ቀናት እንዲሆኑ ዘንድም ነው።

ይህንን በጥልቅ ለመረዳት፣ በዛሬው ዕለት በምንፈጽመው አመድ የመነስነስ ሥርዓት ዘንድ ያሉትን ሁለት ነገሮችን እንመልከት፦ አንደኛው ተለወጡ በወንጌልም እመኑ ይላል፣ ሁለተኛው አፈር መሆንህን አስታውስ ወደ አፈር ትመለሳለህ የሚለው ነው።

የመጀመሪያ ጥሪ ለንስሐ ነው። መለወጥ ያለበት በአፍአዊ ኑሮአችን የምናሳየው ሕይወት ሳይሆን፣ ንስሐ መግባት መለወጥ ማለት፣ የሕይወት አቅጣጫን መለወጥ ያመለክታል። ትናንሽ ነገሮችን በመለወጥ ሳይሆን አጠቃላይ/ ሥር ነቀላዊ መለወጥን ያመለክታል። ንስሐ መግባት መለወጥ ማለት የምትከተለውን ፈሪሳዊው የኑሮ ዘዴ የሚቃረን መንገድ መምረጥ ማለት ነው። ይህ ፈሪሳዊ የኑሮ ዘዴ ሁሉ ጊዜ ስሜታችን በመቆጣጠር ሲያሳስተን ይኖራል። የኃጢአት ባሮች ያደርገናል፣ ለይስሙላ በመኖር ለብ ያለ ሞራላዊ ሕይወት እንዲኖረን ያደርጋል።

ንስሓ መግባት ግን ከፍ ያለውን የክርስትና ሕይወት በመምረጥ ዘለዓለማዊው ቃለ በሆነው በኢየሱስና በወንጌል እንድንኖር ይረዳናል። የመለወጥ ግብ የኢየሱስን ሕይወት በመከተል እርሱ እራሱ የሕይወት መንገድ በመሆኑ በእርሱ መራመድ በብርሃኑ እንድንመራ ልባችን በመክፈት ጉዞአቸን በሚያንቀሳቅስ ኃይሉ መራመድ ነው።

በዚህ መንገድ አስደናቂውን የንስሐ ፍሬ ማግኘት እንችላለን። ንስሐ መግባት የኑሮአችን ዘዴ የምንለውጥበት ቀለል ያለ ግብረ ገባዊ ውሳኔ ምውሰድ ብቻ ሳይሆን፣ ከተጨባጭና ነዋሪ የሆነው ከክርስቶስ ግር በሙላት የሚያዋህደን የእምነት ምርጫ ነው።

መለወጥ እና በወንጌል ማመን ሁለት የተለያዩ ነገሮች አይደሉም። መለወጥ ሲባል መንገድ እውነትና ሕይወት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያቀርብልን ጥሪ ብቸኛ አዳኝ እርሱ መሆኑ በልብ ሙላት እሺ ብሎ መቀበልን ያመለክታል።

በወንጌላዊ ማርቆስ “ጊዜው ደርሰዋል፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እነሆ ቀርባለች፣ ንስሐ ግቡ/ተለወጡ በወንጌልም እመኑ” በሚል የደህንነት ጥሪ መልእክቱን ይጀምራል።

ይህ መለወጥ እና በወንጌል ማመን የክርስትና ሕይወት መጀመሪያ ብቻ ሳይሆን የመላ ሕይወት ጉዞ ሸኝ ነው። በክርስትና ሕይወት ጉዞ፣ እያንዳንዱ ቀን ለንስሐ ይጠራናል፣ በእርሱ እንድንተማመን ይጠይቀናል፣ ሕይወቱን በመካፈል ከእርሱ ጋር አንድ እንድንሆን ይጋብዘናል፣ እውነተኛ ፍቅርን ከእርሱ እንድንማር እና የእግዚአብሔር ፈቃድ ለመፈጸም በየዕለቱ እንድንከተለው ይማጠናል።

በየዕለቱ ድካም ችግር መውደቅ ቢፈራረቅብንም የክህደት ፈተናም ቢያጋጥመንም ወደ ልባችን መለስ ብለን የእየሱስ መንገድ በመከተል ከራስ ወዳድነት ተላቀን ሌሎች የግል ችግሮቻችንን ትተን በክርስቶስ ለእግዚአብሄር ፍቅር ልባችን በመክፈት በትሕትና በፍቅር እንድንኖር ተጠርተናል።

ዘንድሮ ለአርባ ጾም ባስተላለፍኩት መልእክት ከእኔነት ነፃ አውጥቶ በፀጋው እራሱን የሚሰጠን አዳኝ የግድ ለመቀበል ትሕትና ያስፈልጋል ብዬአለሁ። ይህ በሚሥጢረ ንስሐ ቅዱስ ቍርባን እውን ይሆናል። የክርስቶስ ፍቅር ምስጋና ይድረሰው እና እኛ ትልቅ ጽድቅ በሆነ ፍቅር ለመሳተፍ እንችላለን። ባለ ዕዳዎች ሆነን ሳለን ዕዳችንን ከሚገባን እና ከምንጠብቀው በላይ በዚሁ ጽድቅ ተሳታፊነት ምክንያት ተቀብሎልናል።

የተመረጠው የፀጋ ጊዜ የሆነው የአርባ ጾም ጊዜ በጥንታዊው “አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ” የሚል ቃል ትክክለኛው መንፈሳዊ ትርጕሙ ይገለጣል።

ይህ ጥቅስ ወደ አባታችን አዳም ይወስደናል አባታችን አዳም የእግዚአብሔር ትእዛዝ በተላለፈ ጊዜ እንጀራህ በፊትህ ላብ ትበላለህ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ አለው።

ይህ የእግዚአብሔር ቃል ምንኛ ያክል ወዳቂዎች በሌላው አነጋገር ሟቾች መሆናችንን ያስታውሰናል። የአርባ ጾም ሥርዓት አምልኮ በአንድ በኵል ለሐቅና ለጥበብ እየጠራን ሞትን ያስታውሰናል፣ በሌላው በኵል ደግሞ የክርስትና እምነት በሞት ከሞት ነፃ ያወጣንን ክርስቶስን እንድንመለከት ይጠራናል። የሰው ልጅ ዐፈር ነው። ወደ ዐፈርም ይመለሳል። ይህ ዐፈር ግን እግዚአብሔር ላለ መሞት ስለ ፈጠረው ክቡር ዐፈር ነው። ይኽም አዲሱ አዳም ክርስቶስ ነውና። ክርስቶስም ይኸንን ዐፈርነት በመስቀል ላይ በመሞት ከፈለው።

የአዳም ልጆችን ገዝቶ የነበረው ሞት በክርስቶስ ትንሣኤ አከተመ፣ መለኮታዊ ጸጋም ተላበሰ ከሥጋ ትንሣኤ በኋላ ወደ ሚቀጥለው ሕይወት ተሻገረ።

ዓመድ የመነስነሱ ሥነ ሥርዓት በአርባ ጾም ጊዜ በኢየሱስ ሕማማት ሞትና ትንሣኤ በመስጠም እንድናስተነትን የሚጠራ ትንሽ ምልክት ነው።

ኢየሱስን ለመከተል በጥፎ ነገር ለማሸነፍ ጥሩ ነገርን ለመምረጥ ኃጢአተኛው አሮጌው ሰውነታን እንዲሞት ትተን አዲስ በፀጋ የተወለደውን አዳም እንዲወለድ በኢየሱስ ሕማማት እና ትሩፋት እንድንለወጥ ቃል የምንገባበት ምልክት ነው። በዚሁ ጉዞ የእመቤታን ድንግል ማርያም ጥበቃና እርዳታ አይለየን።








All the contents on this site are copyrighted ©.