2010-02-17 14:17:10

እግዚአብሔር መልካም እንጂ መልካም አድራጊነት ኣይደለም


ፖፖሊ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የእየሱሳውያን ማኅበር ወርኅዊ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ኣባ ስቴፋኖ ፈሚኒስ ስደተኛው እና ተዋህዶ የመኖሩ ጉዳይ በተመለከተ ባቀረቡት ሰፊ ሓተታ፣ እግዚአብሔር መልካም እንጂ RealAudioMP3 መልካም አድራጊነት ኣይደለም፣ እግዚአብሔር በባለቤትነት ደረጃ ደግ ነው የእግዚአብሄር ደግነት ቅጽል እንዳልሆነ መሠረት በማድረግ፣ ክርስትያኖች ገራገሮች እና ዝም ባዮች አይደሉም የክርስትናው ደግነት ከፖለቲካዊ ጽንሰ ሀሳብ የተወለደ የዋኅነት ማለት አይደለም፣ ለድኾች ለተናቁት ለተረሱት ለተገለሉት ወላጅ አልባ ለሆኑ የሚቆም ክርስቶሳዊ ፍቅር የሚኖር ማለት ነው ብለዋል።

ይኸንን መሠረታዊ ሀሳብ በማስደገፍ በቅርቡ ክርስትያኖች ገራገሮች ናቸው የሚል ቅጽል ስም ለሰጡዋቸው የፖለቲካ አካላት መልስ ሲሰጡ ደግነት የፈሪሳዊነት መንፈስ የሚስከተል እዩልኝ እወቁልኝ የሚል ተግባር አይደለም፣ በተለያዩ ከተሞች እና አገሮች ቤተ ክርስትያን የድጋፍ ተቋሞችዋ አማካኝነት አለ ልዩነት እና አድልዎ መስተንግዶ እና ሰብአዊ፣ መንፈሳዊ ስነ አእምሮአዊ ድጋፍ ታቀርባለች። ስለዚህ ክርስቶስን መመስከር በዚህ ተግባር የተሸኝም ነው። በርግጥ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ተቋም አይደለችም ሆኖም በክርስቶስ ፍቅር ተገፋፍታ ግን ግብረ ሰናይ ታቀርባለች። ይህ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍቅር በሓቅ በተሰኘቸው አዋዲት መልእክታቸው ሰፋ በማድረግ ተንትነውታል። የቤተ ክርስትያና የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት እንደሚያረጋገጥልን ካቶሊክ ምእመናን ገራገር ሳይሆኑ በተጨባጩ ዓለም የሚኖሩ መሆናቸው በጥልቀት ያስረዳል፣ ስለዚህ በሁሉም በፖለቲካው በኤኮኖሚው በማኅበራዊው ጉዳይ እንዲሁም በትምህርት ዘርፍ ጭምር የማኅበራዊ ትምህርትዋ ታንጸባርቀዋለች ካሉ በኋላ የኤሮጳው ባህል ክርስትያናዊ መሠረት ያለው ነው፣ ሲባል ምን ማለት ነው? ጸረ ሌላው ሃይማኖት መቆም ማለት አይደለም፣ እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን የተናቀ ድኻ ሆኖ ወደዚህች አለም ሥጋችን ለብሶ መምጣቱ የሚያረጋገጠው ወንጌላዊ ቃል የሚያንጸባር ማለት ነው። ስለዚህ ይኸንን የተረዳ ሌላውን ለመቀበል አይፈራም ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.