2010-02-17 14:12:18

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ዓለም አቀፍ የጥሪ ቀን


ካህን ታማኝ እና እውነተኛ ምስክር ለመሆን ከክርስቶስ ጋር የጠበቀ ጓደኝነት ሊኖረው ይገባል፣ በሚል ሀሳብ ላይ የጸና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ፓ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ሁሌ በያመቱ ሚያዝያ 25 ቀን የላቲን ሥርዓት የምትከተለው RealAudioMP3 ቤተ ክርስትያን የመልካም እረኛ በዓል ከምታከብርበት ዕለት ጋር በማያያዝ ለሚታሰበው ዓለም አቀፍ የጥሪ ቀን ምክንያት መልእክት ማስተላለፋቸው ተረጋገጠ።

በዚህ 47ኛው ዓለም አቀፍ የጥሪ ቀን ኅያው ምስክርነት ጥሪን ያነቃቃል በሚል መሪ ቃል የሚታሰብ መሆኑ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን የሚያስተላልፉት መልእክት ትላትና በይፋ መቅረቡ ተገልጠዋል። ካህናት እየተስፋፋ ላለው አለ እግዚአብሔር የመኖሩ ሂደት የሚቃወሙ ምልክቶች ናቸው ብለዋል። በመልእክቱ የጥሪ ፍሬያማነት በእግዚአብሔር ነፃው ፍቃድ ላይ የጸና መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማስመልከት፣ በሌላው ረገድ የተጠሩ የሚሰጡት በማኅበር እና በግል የሚገለጥ ኅያው ምስክርነት፣ ለጥሪ መበራከት አቢይ አስተዋጽኦ እንዳለው አሥምረውበታል። ካህናት አለ ምንም ማመንታት በሙላት ለወንጌል ታማኝ ሲሆኑ፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን የቁሳዊነት ባህል አመጣሽ ለሚኖር ራስ ወዳድነት የሚያነቃቃ ግለኝነት ለሚያስፋፋው ልቅ ባህል የሚቃወም ምልክት ሆኖው ይገኛሉ፣ ስለዚህ የመናንያን ወይንም የጥሪ ሕይወት ክርስቶስን መምሰልን እና እራስን በእርሱ መለየትን ይጠይቃል። ይህ ማለት ደግሞ በሕይወት እና በሰብአዊ ታሪክ ዘንድ ለእግዚአብሔር ቀዳሚው ሥፍራ መስጠት ማለት ነው ብለዋል። በዚህ መንፈስ የሚኖር እወነተኛው ጥሪ፣ ብዙዎች ከክርስቶስ ለሚቀርብላቸው ጥሪ በቸርነት እራሳቸው ለመለገስ ያነቃቃቸዋል ብለዋል።

ስለዚህ የቅዱስ አባታችን መልእክት የጥሪ መሠረት ከክርስቶስ ጋር የሚመሠረት ጓደኝነት መሆኑ ያብራራል። ካህን የእግዚአብሔር ሰው፣ እራሱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ሲሆን፣ እግዚአብሔር በሌሎች ይፈቀርም ዘንድ ይደግፋል። ለእግዚአብሔር ቃል ልቡንና ጀሮውን ሁለመናውን ከሰጠ በእርሱ ፍቅር ተማርኮ ፍቅሩን ይኖራል። በመቀጠል ጥሪ እራስን ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት መሆኑ በማብራራት፣ እራስን ለእግዚአብሔር መስጠት ለሌሎች እራስን አሳልፎ ለመስጠት ሚዛን ነው። እራስን በሙላት ለእግዚአብሔር ካልሰጡ ስለ ሌሎች እራስን አሳልፎ መስጠት የሚደረገው ጥረት ሙላት እንደማይኖረው ገልጠዋል። የክህነት ጥሪ እለት በእለት ከክርስቶስ ጋር አብሮ መጓዝን ይጠይቃል፣ በሶስተኛ ደረጃ ካህን እግዚአብሔር ከሰጠው መንጋ የማይነጠል አብሮት ፊት ቀድሞት በመምራት የሚጓዝ፣ በመንጋው መካከል ልዩነት መከፋፈል አለ መግባባት እንዳይኖር ይቅር መባባልን በቃል እና በሕይወት የሚያስተምር ነው ብለዋል።

ካህናት ተነጥለው ደስታ የሌላቸው ከሌሎች ጋር የማይግባቡ ሀዘንተኞች ሆነው በመጠራጠር የሚኖሩ ከሆነ፣ ወጣቱን የኅብረተሰባችን ክፍል ክርስቶስን ለመከተል እንዴት ሊቀሰቅሱ ይችላሉን? የሚል ጥያቄ በማቅረብ ካህናት ክህነት ያለው ጥልቅ ውበት ማንጸባረቅ ይኖርባቸዋል፣ ለጥሪ ታማኝ የሆነ ካህን ገዳማዊ ክርስቶስን ማገልገል የሚሰጠውን ደስታ ስለ ሚመሰክር ሁሉም ለቅድስና መጠራቱን የሚያረጋግጥ ምልክት ሆኖ ይገኛል በማለት ያስተላለፉት መልእክት ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.