2010-02-17 14:15:24

ሃዪቲ፦ የተፈጥሮ አደጋ ክስተት


በሁሉም የመገናኛ ብዙሃን እንደተመለከተው ሃዪቲ ባለፈው ወር በኃይለኛ ርእደ መሬት መጠቃቷ የሚዘከር ሲሆን፣ በሰው እና በንብረት ላይ ያስከተለው ጉዳት የዓለም ሕዝብ ለዚህች አገር እጁን ይዘረጋ ዘንድ ማነቃቃቱ RealAudioMP3 ሲረጋገጥ፣ ይህ በእንዲህ እንዳለም በአገሪቱ ባለፉት ቀናት የጣለው ኃይለኛው ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሳቢያ በርእደ መሬቱ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረው ኬፕ ህይቲያን የሚገኘው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተደርምሶ አራት ተማሪዎች ሕይወታቸው ሲያጡ ሌሎች ሁለት የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የክልሉ የአደጋ የመከላከያ ፈጥኖ ደራሽ ጽ/ቤት ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።

ሃዪቲን እና በዚህች አገር የሚገኙት የሳሊዚያን ማኅበር ካህናት እና ደናግል በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የሳሊዚያን ማኅበር ጠቅላይ አለቃ ኣባ ፓስኳለ ቻቨስ ቪላኑዌቫ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ለዚህች አገር እየቀረበ ያለው ድጋፍ እና ትብብር እንዲሁም የእርዳታው ስርጭት እጅግ ፈጣን በሆነ አሠራር እየተከናወነ መሆኑ ቀርበው ለማረጋገጥ መቻላቸው በመጥቀስ፣ የሃዪቲ ሕዝብ በጠና ድኽነት የተጠቃ ሆኖ እያለ ርእደ መሬት ባስከተለው አደጋ ሳቢያ የነበረውን ትንሽ ንብረት በማውደም እና የብዙ ሕይወት ለሞት በመዳረግ፣ ብዙዎች አለ መጠለያ በማስቀረት ድኽነቱ እንዲባባስ ማድረጉ ገልጠው፣ ቤተ ክርስያን ባላት በተለያዩ የግብረ ሰናይ ማኅበሮችዋ እና መንፈሳዊ ማኅበራት አማካኝነት ከሃዪቲ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ለሃዪቲ ሕዝብ ቅርብ መሆኗ በቀዳሚ ደረጃ በቃል እና በተግባር እየመሰከረች ነው ብለዋል። ሃዪቲ ዳግም የመወለድ መብት አላት ስለዚህ ይኽ መብት ይከበርላት ዘንድ የሁሉም ትብብር እና ድጋፍ ወሳኝ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.