Home Archivio
2010-02-17 14:14:10
27ኛው ዓለም አቀፍ ዕለተ ህሙማን
ባለፈው ዓርብ የሕክምና ባለ ሙያዎች ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዝይግሙንት ዞሞውስኪ ዓለም ዓቀፍ የህሙማን እለት ምክንያት በማድረግ፣ በዋና ጸሓፊዎቻቸው
ብፁዕ አቡነ ኾሰ ረድራዶ እና በብፁዕ አቡነ ማሪኡስዝ ጊየርስ ታጅበው ሮማ ከተማ የሚገኘውን ቅዱስ መንፈስ የሕክምና መስጫ ማእከል መጎብኘታቸው ሲገለጥ፣ የሮማ የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት አስተዳዳሪ ሓኪም ማውሮ ጎለቲ ጉብኝቱ ብፁዓን አቡናት በሆስፒታሉ ተገኝተው የህክምናው ማእከል ያለውን የሕክምና መስጫ ክፍሎች በመዘዋወር ብቃቱን የሚያስመሰክር በዕደ ጥበብ የተካነ ዘርፎችንም በመጎብኘት፣ በሆስፒታሉ የሚገኙትን ህሙማን በመጠየቅ እና አብሮ በመጸለይ የተከናወነ መሆኑ በመግለጥ፣ የሕክምና ሙያ ቴክኒካዊ ብቃት የሚያረጋገጠው ብቻ ሳይሆን ጥሪም ጭምር መሆኑ ብፁዕ አቡነ ዚሞውስኪ ሆስፒታሉን በመጎብኘት ለህክምና ባለ ሙያዎች ባሰሙት መልእክት ማሳሰባቸው ሓኪም ማውሮ ጎለቲ አስታውቀዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.