2010-02-12 11:48:56

የኤውሮጳው ህብረት፣ የሴቶች መብት ውሳኔ?


የኤውሮጳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እኵልነት እና የሴቶች ሰብአዊ መብት ውሳኔ በማስመልከት ያጸደቀው ሰነድ በማስደገፍ በዚሁ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማልታ ወኪል ሲሞን ቡሱቲል ፖከቲካዊ እና መዋቅራዊ፣ ማኅበራዊ RealAudioMP3 እና በባህል መሠረ ሲተነትኑት፣ በውስጡ ጸረ ሕይወት ማለትም የሴቶች ጤንነት ጥበቃ በሚል ምክንያት፣ ጽንስ ማስወረድ የሚፈቅድ ወይንም በሕግ የተከለከለ እንዳይሆን የሚገፋፋ፣ የሚወለደው የሕፃን መብት የሚጥስ ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ስለዚህ ይህ ውሳኔ ውድቅ ለማድረግ በስነ ባህል የተደገፈ እሴቶችን የሚያረጋገጥ ባህላዊ ትግል ማነቃቃት ግድ ነው። የሞት ባህል በሕይወት ባህል ላይ ድል መንሳት አለበት። ይህንን ለማድረግ የባህል የውይይት መድረኮች ማነቃቃት አስፈላጊ ነው። ስለ ሕይወት በተመለከተ የእያንዳንዱ አባል አገር ያለው ባህላዊ አመለካከት መጣስ የለበትም፣ እንዳውም የሕይወት ባህል በኤውሮጳ ህብረት ደረጃ ዋስትና ማግኘት ይኖርበታል እንዳሉ ሲር የዜና አግልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.