2010-02-12 11:52:15

የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ወጣቶች


የኮሎምቦስ መንፈሳዊ የፈረሰኞች ማኅበር ከማርያም የካህናት ማኅበር ጋር በመተባበር ስለ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ወጣቶች እና እምነት በሚል ርእስ ሥር ያካሄዱት ጥናት መሠረት እንደሚያመለክተው፣ ከአገሪቱ RealAudioMP3 ወጣት ካቶሊክ ብዛት ውስጥ 85% በእግዚአብሔር የሚያምን፣ ከነዚህም ውስጥ 66% ጽንስ ማስወረደ ኢሞራላዊ ውሳኔ እንደሆነ የሚያምን፣ 63% ጣፋጭ ሞት የሞት ባህል ነው የሚል እና 80% ደግሞ ሃይማኖት እጅግ አስፈላጊ ነው ብሎ እንደሚያምን ለማወቅ ተችለዋል።

የኮሎምቦስ መንፈሳዊ የፈረሰኞች ማኅበር ክቡር በላይ አለቃ አንደርሶን ይላሉ፣ የዚህች አገር ካቶሊክ ወጣቶች በተመለከተ የተካሄደው ጥናት ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን አቢይ ግምት ልትሰጠው እንደሚገባ በማሳሰብ፣ ይህ ደግሞ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመን የሆነው የዚህች አገር አዲስ ትውልድ፣ ለቤተ ክርስትያን እና ለቤተ ክርስትያን ትምህርት ቅርብ እንዲሆን የሚደረገው ሓዋርያው ግብረ ኖልዎ የሚያበረታታ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.