2010-02-12 11:40:23

የስነ ሕይወት ስነ ምግባር እና ባኅርያዊ ሕግ


ትላትና ከሰዓት በኋላ በቫቲካን ጳጳሳዊ የሕይወት ተቋም ያዘጋጀው 16ኛው የስነ ሕይወት ስነ ምግባር እና ባኅርያዊ ሕግ ይፋዊ ጉባኤ መጀመሩ ከቅድስት መንበር የተላለፈ መግለጫ አረጋገጠ። RealAudioMP3

የጳጳሳዊ ስነ ሕይወት ተቋም ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊሲከላ ስለ ዓውደ ጥናቱ በማስመልከት ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ነገ ተጋባእያኑ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጋር እንደሚገናኙ በመግለጥ፣ ይህ 16ኛው የስነ ሕይወት ተቋም ያዘጋጀው ዓውደ ጥናት፣ ስለ ስነ ሕይወት ሥነ ምግባር የእያንዳንዱ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ስለዚህ ዓቢይ ርእሰ ጉዳይ የሚሰጡት የተለያዩ አመለካከቶች እና ያለው ኃላፊነት፣ በጋራ ውይይት የሚደረግበት ሳይሆን፣ የሀሳብ ልዩነት በማጤን ነገር ግን በመደጋገም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንዳሉት ባኅርያዊ ሕግ፣ የሰው ልጅ ወይንም የቤተ ክርስትያን ፈጣራ ሳይሆን በእያንዳንዱ ሰው ልጅ ብሎም በተፈጥሮ ዘንድ የታተመ መሆኑ በስነ አመክንዮ ለማበከር ጥረት የሚደረግበት መድረክ ነው ብለዋል።

ባኅርያዊ ሕግ ወይንም ሥርዓት ክርስትና ከመጀመሩ በፊት የግሪክ ሊቃውንት የቺቾሮነ ድርሰቶች የሮማ ሕገ መንግሥት ለይተው ያብራሩት ነው። ስለዚህ የክርስትና ፈጠራ ሳይሆን በያንዳንዱ ሰው ዘንድ እና በተፈጥሮ የታተመ አብሮ የተፈጠረ የመፈጠራችን መንትያ ነው፣ ስለዚህ ይህ ባኅርያዊ ሕግ ለመጻረር የተፈጥሮ ሥርዓታዊ ሂደት ማወክ ማለት ነው ሲሉ ስለ ጉባኤው በማስመልከት የሰጡት ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.