2010-02-12 17:57:27

እግዚአብሔር ሙሉውን ሰው ማዳን ይፈልጋል


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት ሓሙስ የሉርድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዝክረ በዓልና፣ አሥራ ስምንተኛው የዓለም ሕሙማን ቀን ምክንያት በማድረግ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ብዙ ምእመናን እና ሕሙማን የተሳተፉት መሥዋዕተ ቅዳሴ አቅርበዋል። RealAudioMP3
በቅዳሴው ሥርዓት በዓሉን ለማድመቅ ባለፈው ሳምንት ከሉርድ ወደ ሳንታ ማርያ ማጆረ ባዚሊካ ተዛውሮ ምእመናን ሲሳለሙትና ሲጸልዩበት የሰነበተው የቅድስት በርናርደት ሲቡሩ ቅዱስ አጽም ከካስተል ሳንታአንጀሎ ጀምሮ በተዘጋጀው ኡደት ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ተዛውሮ ተጸልዮበታል። ቅዱስነታቸው በቅዳሴው ሥርዓት ባሰሙት ስብከት በቤተ ክርስትያን ሕሙማንና ሥቃያተኞች የፍቅር ተአምር ምስክሮች እና ምሳሌ ናቸው፣ ቤተ ክርስትያን ብሥቃይ ላይ ላሉት ሁሉ አሁንም የእግዚአብሔር ፍቅር ምሕረትና ጥናት ትለምናለች ሲሉ አረጋግጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.