2010-02-12 11:46:28

ለክርስትያን አንድነት መረጋገጥ


በተለያዩ ክርስትያን ማኅበርሰብ መካከል አንድነት እንዲረጋገጥ የተጀመረው የጋራው ውይይት 40ኛው ዓመት ማገባደዱ የሚዘከር ነው። ይኸንን የአርባ ዓመቱን የውይይት ሂደት ለመገምገም እና ቀጣዩ የጋራው ውይይት RealAudioMP3 ፈር ለማስያዝ እዚህ ሮማ በሚገኘው በተለያዩ ማኅበረ ክርስትያን መካከል አንድነትን የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ መካሄዱ ተገለጠ። ይህ ትላትና የተፈጸመው ጉባኤ በማስመልከት የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ክቡር ጳጳስ ቶም ራይት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን ጠቅላላ የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን በተለያዩ ችግሮች የተጠቁ እና መከፋፈል የሚታይበት፣ ድኅረ የዘመናዊነት ባህል ያመጣው፣ ሁሉም ሁሉን የሚጻረር ሀሳብ የሚያቀርብበት በመሆኑ፣ ሥልጣን በተሞላው በቤተ ክርስትያን ስም እና አንደበት እንዲሁም በሁሉም ስም የሚናገር ማን ነው? በአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን እንዲሁም በፕሮተስታንት እና ከዚህች ቤተ ክርስትያን በተነጠሉት አቢያተ ክርስትያን ዘንድ የሚታይ ችግር ነው። ባህላውያን ስር ነቀላውያን የግራ እና የቀኝ፣ ወግ አጥባቂዎች እየተባለ የሚታየው መከፋፈል በአቢያተ ክርስትያን ዘንድን ይታያል፣ በአንዲት ቤተ ክርስትያን ዘንድ ያለው ልዩነት ማስወገድ ለአቢያተ ክርስትያን አንድነት ወሳኝ ነው። አንዲት ቤተ ክርስትያን በውስጥዋ ያለውን መከፋፈል በማጤን መፍትሄ በመሻት ለመላይቱ ቤተ ርክስትያን አንድነት እና ውህደት መቆም አለባት። ውስጠ መከፋፈል ማስወገድ ተቀዳሚ ዓላማ መሆን አለበት ብለዋል።

የዛሬ አርባ ዓመት በፊት የዘመናዊነት ህልም የጎላበት ሁሉም አንድነት ምንኛ ደስ የሚያሰኝ መሆኑ ያነጣጠረበት ወቅት ነበር። ይህ ደግሞ ልክ የዛሬ አንድ መቶ ዓመት በፊት ልኡካነ ወንጌል ክርስቶስስ ለመላ ዓለም ለማበሰር መሠረታዊው አንድነት ካጎሉበት ዘመን ጋር የሚመሳሰል ነው። ሆኖም ግን የሃያኛው ክፍለ ዘመን ማኅበራዊ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ክስተቶች ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ እና በዚህ ጦርነት ሳቢያ መከፋፈል መለያየት ጎልቶ በአሁኑ ወቅት የምንኖርበት ዓለም የዚህ የመከፋፈል ባህል ውጤት እንዲሆን አድርጎታል፣ ይህ ደግሞ ወደ አቢያተ ክርስትያን ዘንድ ጭምር ያዘገመ ባህል ነው። ስለዚህ መከፋፈል እና መለያየት ለማስወገድ መወያየት ቀላል አይደለም፣ ይህ ለገዛ ራሱ አቢይ ውጤት መሆኑ የዛሬ 40 ዓመት በፊት አንድነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ውይይት ምስክር ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.