2010-02-10 18:50:10

በሰነጋል የቅድስት በኪታ ዝክረ በዓል ተስታወሰ


ባለፈው ሰኞ የቅድስት በኪታ በዓል ነበር፣ በመላው ቤተ ክርስትያን ታስቦ ቢውልም በሰነጋል ግን ለየት ባለ ተስታውሶ እንደዋለና በዓሉን እሁድ እንዳከበሩት ከቦታው የደረሰን ዜና ያመልክታል። እሁድ መሥዋዕተ ቅዳሴውን የመሩት በሰነጋል የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ እንደራሴ ብፁዕ አቡነ ማርያኖ ሞንተማዮር ናቸው። የበዓሉ መሥዋዕተ ቅዳሴ የተካሄደበት ቦታ ሃን በሚባል ቍምስና ነው፣ ቍምስናው ገና በመገንባት ላይ ያለ ሆኖ ታዳጊያቸው ቅድስት በኪታ ናት። በበዓሉ ላይ ቃለ እግዚአብሔር ያሰሙ ኣባ ዛቭየር ቅድስት በኪታ እአአ የካቲት 8 ቀን 1947 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት መለይታቸውን አስትውሰው ከሱዳን እንደ ባርያ ተሽጠው በአገልግሎት ላይ እያሉ ክርስትና መቀበላቸው፣ በገዳም ገብተው መንኩሰው ለቅድስና መብቃታቸውን ከገልጡ በኋላ የቍምስናው ምእመናን በተለይ ወጣቶች አብነትዋን እንዲከተሉ አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.