2010-02-10 18:48:08

18ኛ ዓለም አቀፍ የሕሙማን ቀን


እአአ የካቲት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በመላው ዓለም የሕሙማን ቀን ይከበራል፣ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በዕለቱ በሮም ሰዓት አቆጣጠር 10.30 በቫቲካን ባዚሊካ መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ በዕለቱ የሉርድ ብፅዕት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓልም ተስታውሶ ይውላል። የዘንድሮው የዕለተ ሕሙማን መሪ ቃል “ቤተ ክርስትያን ለሚሰቃዩት የምታበረክተው የፍቅር አገልግሎት” የሚል ነው፣ ከአሁን በፊት ቅዱስነታቸው በሕመምና በስቃይ የሚገኙ የሰው ልጆች ክብርን አስመልክተው ብዙ ትምህርት ሰጥተዋል። ለምሳሌ እአአ ታሕሣሥ 2 ቀን 2007 ዓም በቅዱስ ዮሓንስ መጥምቅ ሆስፒታል ይህንን ብለው ነበር፣ “ለምን እንሰቃያለን፤ የሥቃይ ሕይወት አዎንታዊ ትርጓሜ ሊኖረው ይችላልን፤ ከሥቃይ ከሞት ነፃ ሊያወጣን የሚችል ማን ነው፤ እነኚህ የኑሮ መሠረታዊ ጥያቄዎች ናቸው። ሥቃይ በአእምሮ ሊታወቅ የማይቻል ምሥጢር ስለሚያኖር፣ እነኚህ ጥያቄዎች በሰው ልጅ አነጋገር ብዙውን ጊዜ መልስ አይገኛቸውም። ይህ ግን ሥቃይ ትርጉም የለውም ማለት አይደለም። በሕመምና በሥቃይ በምንገኝበት ጊዜ እግዚአብሔር ምሥጢራዊ በሆነ መንገድ ይጐበኘናል፣ ሁሉመናችን ለፈቃዱ የተውነው እንደሆነ የፍቅሩን ችሎታ መጣም እንችላለን፣ ብለው ነበር። ነገ በሚካሄደው ሥርዓት ቅዱስነታቸው ከሕሙማን ጋር ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ እንዲሁም ሁል ጊዜ በዚህ አጋጣሚ እንደሚያደርጉት 18ኛው ዓለም አቀፍ የሕሙማን ቀንን የሚመለከት መልእክታቸውን ያስተላልፋሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.