2010-02-08 14:50:33

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የጦም መልእክት ይፋ ሆነ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለጾም ያስተላለፉት መልዕክት ትናትና ረፋድ ላይ በቫቲካን ማኅተም ክፍል ይፋ ሁነዋል። መልዕክቱ ለመገናኛ ብዙኅን ያስተዋወቁት የኮር ኡኑም የተዋሀደ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ፁዕ ካርዲናል ዮሴፍ ኮርደስ ናቸው።

የቀድሞ የኤውሮጳ ምክር ቤት ፕረሲዳንት እንዲሁም በጀርመን የኮንራድ አደንአወር ድርጅት ሊቀ መንበር ሃንስ ገርት ፖተሪንግ በዚሁ ጋዜጣዊ ገለጣ መገኘታቸው ይታወቃል።

የቀድሞ የኤውሮጳ ምክር ቤት ፕረሲዳንት ሀንስ ገርት ፖተሪንግ በዚሁ ግዜ እንዳመለከቱት

ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ጥምረት በተከሰተበት ድኽነት ግሀድ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ኤውሮጳ አዲስ የትብብር መንፈስ ያሻታል።

ሃንስ ገርት ፖተሪንግ ኤአአ 1967 ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ፖፑሎሩም ፕሮግረስዮ የህዝቦች እደገት በተባለ ሐዋርያዊ መልእክታቸው ያስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክታቸ እድገት ሌላ የሰላም መጠርያ ነው ያሉትን አስታውሰው፡ ሐረጉ አሁንም ቢሆን ከፈተኛ አስፈላጊነት እንዳለው መግለጣቸው ተመልክተዋል።

የቀድሞ የኤውሮጳ ምክር ቤት ፕረሲዳንት እና የኮንራድ አደናወር ድርጅት ሊቀመንበር ሀንስ ገርት ፖተሪንግ በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ አያይዘው እንደገለጹት ፡ በፖሊቲካዊ አነጋገር ትብብር ሲባል በንባበ መለኮታዊ ደግሞ ፍቅር ተብሎ እንደሚነገር ጠቅሰው፡ ፍቅር ትብብር እና ወንድማማችነት ተጣምረው በዓለም ላይ ክርስትያኖች ያላቸውን ሐላፊነት እንደሚያንጸባርቁ አስረድተዋል።

ትብብር እና ፍቅር በዓለም ዙርያ የሰው ክብር እና ግርማ ጥበቃ ሐላፊነት መሸከም እንደሚጠይቁም ገልጸዋል።

አርነት እና ፍትሕ የምንፈልግ ከሆነ የምናካሄደው ፖሊቲካ እና ትብብር እና ወንድማማችነት ማእከል ያደረገ መሆን እንደሚጠበቅበትም ሀንስ ገርት ፖተሪን አስገንዝበዋል።

ዓለም አቀፉ የኤኮኖሚ እና ፋይናንስ ቀውሶች እንደተከሰቱ የዓለም ባለ ጠጋ ሀገራት ቀውሱን ለመግታት በርካታ ትሪልዮኖች ገንዘብ ወጪ ማድረጋቸው ያስታወሱት ፖተሪን ሰብአዊ ትብብር በተመለከተ የዓለም ድኽነት ለመቀነስ ግን የተወሰደ ሁነኛ ርምጃ አለመኖሩ ጠቅሰው እዚህ ላይ ወንድማችነታዊ ሰብአዊ ትብብር መጕደሉ ይታያል ማለታቸው ተገልጸዋል።

ኤውሮጳ እና ዓለም አቀፍ ማኅበረ ሰብ ለርሃብ የተጋለጠው የዓለም ህዝብ ከዚሁ ሰቆቄ ለማዳን ግብረ ገባዊ ሐለፊነት አላቸው ያሉት የቀድሞ የኤውሮጳ ምክር ቤት ፕረሲዳንት እና በጀርመን የኮንራድ አደናወር ድርጅት ሊቀ መንበር ሀንስ ገርት ፖተሪን የኤውሮጳ ሕብረት የተያዝነው ዓመት 2010 እኤአ በዓለም ዙርያ ያንሰራፋው ድህነትን ለመቀነስ ቀዳሚ ዓላማው መሆኑ ማወጁ አስታውሰው በዚሁ መስክ ሁነኛ ርምጃ ይወስድ ዘንድ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

እዚህ ላይ የኤውሮፓ ሕብረት ድህነትን የመቀነስ እቅድ እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ኤውሮጳው አዲስ የትብብር መንፈስ በማለት ለጾም ያስተላለፉት መልእክት ይጣጣማል በማለት ፖተሪንግ ለጥቀው አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት ሁለት ሚልያርድ የዓለም ህዝብ በቀን በአንድ ዶላር ተኩል ገቢ መኖር አቅቶት ለርሃብ በተዳረገበት በአሁኑ ወቅት ይህን ህዝብ ካለው መጥፎ ሁኔታ ማላቀቅ ግድ ይሆናል ያሉት ፖተሪንግ ሁነኛ እና ተጨባጭ ርምጃዎች መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል።

በድህነት ብቻ ሳይሆን በኤች አይ ቪ ኤይድስ ፡ የወባ ወረርሽን እና በሳንባ ነቀርሳ በመሰቃየ ያለ ህዝብም እጅግ ብዙ መሆኑ እና ይህንኑም ለመግታት ኤውሮጳዊ ኣና ዓለም አቀፍ ሁነኛ ርማጅ እንደሚያሻ አስገንዝበዋል።

በዓለም ላይ ፍትህ እና ሰላም ለማስፈን የዓለም ህዝቦች ርስ በርሳቸው ሲተማመኑ እና ሲከባበሩ ሰብአዊ እና የእምነታቸው መብቶች ሲክበሩላቸው እንደሆነ የጠቀሱት ፖተሪንግ ዓለምን በኀይል ለመለወጥ የሚሹ ጽንፈኞችን በጋራ መታገል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በቅድስት መንበር የኮር ኡናም የተዋሃደ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ብፁዕ ካርዲናል ፓውል ዮሴፍ ኮርደስ በበኩላቸው የሰው ልጅ ከፈጠሪው እግዝአብሔር ርቆ እና ተገልሎ ፍትህና ሰላም ለማምጣት እንደማይችል በማስርገጥ ሰው ሁሉኑም የማድረግ ችሎታ እንዳለው በማመን ስህተት በስህተት ላይ ሲፈጽም ይስተዋላል ማለታቸው ተዘግበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.