2010-02-08 14:54:04

ሃዪቲ ወደ ማገገም ብላለች፡


ሃዪቲ ላይ ሳላሳ ሶስት ህጻናት በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገሪቱ ለማስወጣት ሞክረዋል የተባሉ አስር የአመሪካ ዜጎች በፖሊስ መያዛቸው ከዋና ከተማ ፖርት ኦው ፕራንስ የመጣ ዜና አመልክተዋል።

አመሪካውያንኑ አባባሉን ውድቅ ማድረጋቸው እና ርዳታ በመስጠት የተሰማራ ቡድን አባላት መሆናቸው ጠቅሰው ፡ የክሱ መንስኤ ካለ መረዳዳት የተነሳ መሆኑ መግለጣቸው የተነግረዋል’።

ይህ በዚህ እንዳለ ባለፈው ጥር ወር አስራ ሁለት ቀን ሃዪቲ ላይ በተከሰተው የመሬት ነው መጠለያ አልባ የቀሩ ስድስት መቶ ሰዎች በፖርት ኦው ፕራንስ በተተተከለው ግዙፍ ግዝያዊ ተንዳ መጠለላቸው ፡ ሁለት መቶ ሳላሳ አምስት ሺ ሰዎች ወደ ሌሎች ከተሞች መዘዋወራቸው ከቦታው የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም የጣልያን ካሪታስ እና ሌሎች የግብረ ሰናይ ድርጅቶች በፖርት ኦው ፕራንስ እና አከባቢ በተከሉዋቸው ተንዳዎች ለችግር የተጋለጠውን ህዝብ ዕለታዊ ምግብ እየሰጡ መሆናቸው አብሮ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

ካሪታስ ኢንተርናጽዮናሊስ በቅድመ ግንባር የሚሰጠው ሰብአዊ ርዳታ ስኬታማ መሆኑ ከቦታው የደረሰ ዜና ገልጸዋል ።

በመሬት ነውጥ ባልተነኩ የሃዪቲ ክልሎች ትምህርት ቤቶች መከፈታቸው ደሴቲቱ መልሶ ለመገንባት ለጋሽ ሃገራት የሚቀይሱት እቅድ እየተጠበቀ መሆኑ ተገልጸዋል።

ሃዪቲ መልሶ ለመገንባት በብዙ ሚልያርድ ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንደሚያሻ ይህ ከፖርት ኦው ፕራንስ የመጣ ዜና አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.