2010-02-05 13:39:24

ጊኒ፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒ.


እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደካምሉ፣ የሚለውን ወንጌላዊ እውነት መርህ በማድረግ የጊኒ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ለአገሪቱ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒ. እንዲሆኑ ለተመረጡት ዣን ማሪየ ዶረ መልካም RealAudioMP3 የአገልግሎት ሥራ በመመኘት ኃላፊነቱ አስቸጋሪ ቢሆንም ክብር ጭምር ነውና ለማገልገል በተመረጡበተ ኃላፊነት ለሕዝብ እና ለአገር ጥቅም እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር እንዲደግፋቸው የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በተገናኙበት እለት በመጥቀስ በጸሎታቸው እንደሚያስቡዋቸው ማረጋገጣቸው ተገለጠ።

የኮናክሪ ሊቀ ጳጳስ የጊኒ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ቪንሰንት ኩሊባልይ በቁሳዊ ሃብት የተሞላህ ብትሆንም እግዚአብሔር ያልታከለበት ድካም ከንቱ ነው፣ በማለት በተካሄደው ግኑኝነት ይኸንን እንደመሰከሩ ሲገለጡ፣ ጠቅላይ ሚኒ. ዶረ በበኩላቸውም በእግዚአብሔር ቡራኬ ተሸኝተን አገራችንን እናገልግል በማለት፣ አክለውም በአገሪቱ የማይሻረው የሰብአዊ እሰይቶች መሠረት በማድረግ ጊኒን ለማደስ እግዚአብሔር በቡራኬው ይደግፈን እንዳሉ ሲረጋገጥ በተካሄደው ግኑኝነት በጊኒ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ ማርቲን ክረበስ መገኘታቸው ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.