2010-02-05 13:34:22

የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለዓለም ዓቀፍ የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር መልእክት


እ.ኤ.አ. ከየካቲት 12 ቀን እስከ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. በካናዳ ቫንኮቨር ከተማ ለሚካሄደው ዓለም ዓቀፍ የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር ምክንያት ለከተማይቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ሚለር መልእክት ማስተላለፋቸው RealAudioMP3 የቅድስት መንበር መግለጫ አረጋገጠ።

ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት፣ ስፖርት በተለያዩ ሕዝቦች እና በአገሮች መካከል ሰላም እና ወዳጅነትን፣ የሚያነቃቃ የሰላም መሣሪያ ይሆን ዘንድ በማሳሰብ፣ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ስለ ስፖርት እና የስፖርት አስተዋጽኦ፣ በሕዝቦች መካከል ሰላም የተካነው መግባባት እንዲሰፍን የሚያደርግ አዲስ የፍቅር ባህል እንዲረጋገጥ የሚያግዝ መሆን አለበት በማለት ባንድ ወቅት ያሉትን ሃሳብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በማስታወስ፣ በዚህ በቫንኮቨር በሚካሄደው የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር ለሚሳትፉ ስፖርተኞች ይህ የባህል ሂደት የተዋጣለት እንዲሆን በተለያየ መስክ ተጠምደው የሚገኙት የስፖርት ፈደረሽን አስተዳዳሪዎች እና አባላት በጸሎታቸው እንደሚያስቡዋቸው በማረጋገጥ፣ ከወርቅ የላቀ በሚል መሪ ሃሳብ የኦሎምፒክ ስፖርት በሚካሄድበት ወቅት ለሚፈጸመው የሁሉም ሃይማኖቶች የጋራው ለስፖርተኞች እና ለጎብኚዎች መንፈሳዊ እና ሰብአዊ ሓዋርያዊ አገልግሎት ለሚሰጡት እና ይህ የተወጠነው ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የተዋጣለት ይሆን ዘንድ እንደሚጸልዩ በመግለጥ፣ ለሁሉም ስፖርተኞች እና የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር አዛጋጆች ሓዋርያዊ ቡራኬኣቸው በብፁዕ አቡነ ሚካኤል ሚለር በኩል ኣስተላልፈዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.