2010-02-05 13:35:29

ከሥልጣን ሹክቻ እና ፈተና

ለመገላገል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባለፈው ረቡዕ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ ሓዋርያዊ የጉባኤ አዳራሽ የተለመደው ረቡዓዊ ትምህርተ ክርስቶስ ከኢጣሊያ እና ከኢጣሊያው ውጭ ለመጡት በብዙ ሺሕ ለሚቆጠሩት RealAudioMP3 ምእመናን ለወንጌላዊ ግብረ ተልእኮ ቅዱስ ዶመኒኮ የሰጠው ኃይለኛ ግፊት በማብራራት፣ ሁሉም የተጠመደበት ኃላፊነት እና ጥሪ ሥልጣንን በመሻት ከወዲሁ በዚህ ዓይነት መንፈስ የሚታየው ጥሪ የመኖሩ ሂደት በዓለማውያን ምእመናን እና እንዲሁም በቤተ ክርስትያን ውስጥ ማለትም በውሉደ ክህነት እና በገዳማውያን በዓለማውያን ሕዝብ መካከል የሚታይ ፈተና መሆኑ በማብራራት ቅዱስ ዶመኒኮ ከዚህ ፈተና ለመገላገል ያሳየው መንፈሳዊ ብርታት ለሁሉም አብነት ነው ያሉትን ሃሳብ መሠረት የሳን ማሪኖ - ሞንተፈልትሮ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልውጂ ነግሪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ክርስቶስ ወደር የማይገኝለት ዘለዓለማዊ የኅልውናችን ምክንያት የሆነው ፍቅር መሆኑ ቅዱስ ቶማስ ዘ አኵይኖ ሲያብራራ ይህ የማይሟጠጠው በክርስቶስ የተገለጠው ፍቅር ከእግዚአብሔር እና ከሌሎች ጋር የሚያቀራርብ የሚያስተሳስር መሠረት ነው ይላል፣ ይህ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሁሉም ዘርፍ እያስተጋቡት ነው፣ ሌላው ተራ ፍቅር የሚኖርበት የሕይወት ምርጫ በክርስቶስ በተገለጠው መሠረታዊው ፍቅር ላይ ካልጸና እውነተኛ ፍቅር ሳይሆን የግል ፍላጎት ለማርካት የሚመረጥ ኑሮ ነው ብለዋል።

በአንዳንድ የቤተ ክርስትያን ዘርፎች በክርስቶስ ላይ ያለ ፍቅር የደከመ ይመስላል፣ ስለዚህ ለክርስቶስ ያለን ፍቅር ከዛለ ወደ ተራው ፍቅር ካዘነበለ ተራው ፍቅር ውጦን ምስክርነታችን ስብከታችን የፈጠራ ተውኔት ሆኖ ሌላውን የማይማርክ የማያሳምን ቃል ብቻ ሆኖ ይቀራል፣ ስለዚህ ይህ ዓይነቱ የሕይወት ጎዳና ለሥልጣን የመሻት ፈተና ያጋልጠናል፣ የህልውናችን ምክንያት የክርስቶስ ፍቅር መሆኑ ከተረዳን ጥሪያችንን በተገባ ለመኖር እንችላለን ሌላው የሚሰጠን ኃላፊነት የጥሪያችን መግለጫ እንደሆነ አበክረን እንረዳለን ብለዋል። በተለያየ ኃላፊነት ላይ የተቀመጠ ካህን ሊቀ ጳጳስ አቡን በጥቅም ላይ ያላነጣጠረ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር የተቃጠለ መሆን አለበት፣ ይህ ፍቅር ከጎደለ ኃላፊነት ሥልጣን ብቻ ሆኖ ይቀራል። ቅዱስ ፍራንስኮስ ዘ አሲዚ እና ቅዱስ ዶመኒኮ ርእስ በማድረግ ቅዱስ አባታችን ባለፉት ሁለት ረቡእ የሰጡት ትምህርተ ክርስቶስ ፣ ሁለቱ አበይት ቅዱሳት ቤተ ክርስትያንን በውስጥዋ እንድትታደስ ያበረታቱ የቤተ ክርስትያን ተሃድሶ ባህል ያነቃቁ ወንጌልን በሙላት በመኖር ሰብአዊነት የተሞላው ክርስትናን ያበረታቱ መሆናቸው የሰጡት ማብራሪያ ኅልውናችን በክርስትናው ባህል የተመራ በክርስቶስ ፍቅር የተማረከ ማድረግ ከሁሉም ፈተና ነጻ ያወጣናል በማለት የሰጡትን ቃል ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.