2010-02-03 13:44:46

ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን


የካቶሊክ እና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ቲዮሎጊያዊ የጋራው ድርገት በሊባኖስ ያካሄደው ሰባተኛው የውይይት ጉባኤ ወዳጅነት እና ልባዊ መከባበርል በተሞላበት ሁኔታ መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ ይህ ባለፈው እሁድ የተጠናቀቀው RealAudioMP3 በአንተሊያስ ቂልቅያ ከተማ በሚገኘው በአርመን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን መንበር የተካሄደው የጋራው ውይይት፣ የክርስትያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ቫልተር ካስፐር እና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ የዳሚየተ ሜጥሮጶሊ አንባ ቢሾዮ በጋራ የሊቀ መንበርነት ሥልጣን የተመራ እንደነበር ተገለጠ። በውይይቱ መድረክ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ተጠሪዎች፣ የፓትሪያርክ ካቶሊኮስ የሁሉም አርመናውያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን፣ የአርመን ሓዋርያዊት ቤተ ክርስትያን፣ የማላባር ሶሪያዊት ቤተ ክርስትያን ተጠሪዎች መሳተፋቸው ሲገለጥ፣ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን በተካሄደው የጋራው ጉባኤ አለ መሳተፏ ለማወቅ ሲቻል፣ ይህ ሰባተኛው የጋራው ውይይት እ.ኤ.አ. ጥር 27 ቀን 2010 ዓ.ም. የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ተጠሪዎች በተናጥል ባካሄዱት ስብሰባ ተጀምሮ ከጥሪ 28 ቀን እስከ ጥር 30 ቀን የሁለቱም አቢያተ ክርስትያን ይፋዊ የጋራው ውይይት በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መካከል ያለውን ግኑኝነት የሚያብራራ ሰነድ መሠረት በማድረግ ተጀምሮ ድርገቱ ባለፈው ዓመት የቤተ ክርስትያን ባህርይ፣ ሕገ ቀኖና እና ተልእኮ በሚል ርእስ ሥር ተጠናቅሮ የነበረው ሰነድ ዳግም በመመልከት መከናወኑ ለማወቅ ተችለዋል።

የሁለቱም ኣቢያተ ክርስትያን ልኡካን በጋራ ከሊባኖስ ርእሰ ብሔር ሚሸል ስለይማን ጋር እንዲሁም ጥር 28 ቀን የሁሉም አርመን ፓትሪያርክ ካቶሊኮስ ብፁዕ ወቅዱስ አራም አንደኛ ጋር ጭምር መገናኘታቸው ተገልጠዋል። በጉባኤው ፍጻሜ የክርስትያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ቫልተር ካስፐር የተካሄደው ስብሰባ በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የአቢያተ ክርስትያን አንድነት የቲዮሎግያ ሊቃውንት የሚመለከት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚመለከት ነው ካሉ በኋላ፣ ቀጣዩ ስብሰባ እ.ኤ.አ. ከጥር 24 ቀን እስከ ጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው የሁሉም ክርስትያኖች አንድነት በሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሕንጻ እንደሚካሄድ በይፋ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.