2010-02-03 13:48:15

ናይጀሪያ፣ በጆስ ከተማ ስላለው ውጥረት ሁኔታ


እ.ኤ.አ. ጥር 17 ቀን 2010 ዓ.ም. አንድ በማለት በጆስ ከተማ የተቀጣጠለው አመጽ ርእስ በማድረግ በናይጀሪያ ርእሰ ከተማ አቢጃን በሚገኘው በርእሰ ብሔር ሕንጻ በምክትል ርእሰ ብሔር ጉድላክ ሆናዛን ሰብሳቢነት RealAudioMP3 በተካሄደው ስብሰባ የተሳተፉት የጆስ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢግናቲዩስ ካይጋማ፣ ግኑኝነቱ አወንታዊ ነበር እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በተካሄደው የጋራው ውይይት የፕላተአው ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪ የዚህ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ ጆስ መስተዳድር እና የከተማ ነዋሪዎች ማኅበራት እንዲሁም በናይጀሪያ የሚገኙት የአቢያተ ክርስትያን ማኅበር ሊቀ መንበር የአቢጃን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጆን ኣኦናየካ መሳተፋቸውም ፊደስ የዜና አገልግሎት አረጋገጠ።

በጆስ ከተማ የተቀጣጠለው ውጥረት መንስኤ ማህበራዊ ፖለቲካዊ ጎሳዊ ኤኮኖሚያዊ መሆኑ የተካሄደው የጋራው ግኑኝነት በማብራራት፣ ሁሉም በጉባኤው የተሳተፉት የክርስትያን እና የምስልምና ሃይማኖት ተጠሪዎች የተቀጣጠለው ግጭት እጅግ እንዳሳዘናቸው በመግለጥም ድርጊቱን አውግዘዋል። ማንኛውም ዓይነት ውጥረት ሃይማኖታዊ ገጽታ እንዳይለብስ እና የግጭት ተወናያን አካላት ሃይማኖትን ተገን በማድረግ የሚቀሰቅሱት ዓመጽ ሁሉም ሃይማኖቶች በጋራ እንዲቃወሙት ብፁዕ አቡነ ካጋመ ለጉባኤው ባሰሙት ንግግር ማሳሰባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.