2010-02-03 13:45:52

ቅዱስ አጎስጢኖስ ዘ ሂፖ


በተለያየ ወቅት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቤተ ክርስትያን ሊቅ እና አበይት ከሚባሉት የቤተ ክርስትያን አበው አንዱ የሆነው የቅዱስ አጎስጢኖስ ዘ ሂፖ ሕይወት ታሪክ የሚያወሳ የትረካ ፊልም እንዲዘጋጅ RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መስከረም 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ያስተላለፉት የአደራ መሠረት የተዘጋጀው የቅዱስ አጎስጢኖስ ዘ ሂፖ ሕይወት ታሪክ የሚያወሳ ፊልም፣ በኢጣሊያ የራይ ኡኖ የቴሌቭዢን ጣቢያ በኩል ለትርኢት መቅረቡ ሲገለጥ፣ ፊሉም 7 ሚዮን ሕዝብ እንደተከታተለውም የኢጣሊያ የቴሌቪዥን እና የራዲዮ ጣቢያ ጽ/ቤት ያሰራጨው መግለጫ ይጠቁማል።

ይህ ስለ ቅዱስ አጎስጢኖስ ዘ ሂፖ ሕይወት ታሪክ የሚተርከው ፊልም ቅዱስነታቸው በካስተል ጋንደልፎ ገና ይፋ ያልሆነው ቀዳሚውን ክፍል እንዲመለከቱት ቀርቦላቸው፣ ከተከታተሉት በኋላ እጅግ በመርካት ፊልሙ ተጠናቆ ለማየት ያላቸው ጉጉት በመግለጥ፣ ሰብአዊ መንፈሳዊ ሂደት ያጎላ ነው እንዳሉም የሚዘከር ሲሆን፣ የቅዱስ አጎስጢኖስ ዘ ሂፖ የሕይወት ታሪክ የእያንዳንዱ የሰው ልጅ ሰብአዊው እና መንፈሳዊው ገጽታ የሚያጎላ በመጨረሻም እውነትን በማወቅ ሁሉም ሰብአውያን መሰናክሎች እንደሚወጡ የሚያብራራ እና ሁሉም እንደሚያልፍ ነገር ግን የማያልፈው የሁላችን ፍጻሜ የሆነው በፍቅር የተሞላው እውነት እርሱም እግዚአብሔር መሆኑ የመሰከረ ታሪክ ነው እንዳሉም የሚታወስ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.