2010-02-03 13:43:07

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፣ ለአስፍሆተ ወንጌል መጸለይ


ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. በየካቲት ወር ለሚቀርበው ጸሎት ቤተ ክርስትያን የተልእኮዋ መለያ አቅባ በጽናት እና በታማኝነት ክርስቶስን እንድትከተል እና ወንጌልን ለሕዝቦች ሁሉ እንድታበስር የተጠራች መሆኗ RealAudioMP3 እንድትገነዘብ በሚል ሃሳብ የተመራ እንዲሆን በማሳሰብ፣ ሁሉም ምእመናን ለአስፍሆተ ወንጌል እንዲጸልዩ እና በተራቸውም ወንጌልን እንዲያበስሩ የተጠሩ ናቸው ብለዋል።

የቅዱስ አባታችን መንፈሳዊ ጥሪ በማስደገፍ የሳቨሪያኒ ማህበር የልኡካነ ወንጌል ማነቃቂያ ማእከል ሊቀ መንበር አባ ማሪዮ መኒን ከቫቲካ ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የተልእኮ ጥሪ ኵላዊነት መሆኑ የሚያሳስብ ሲሆን፣ ክርስትያን ሁሉ የዚህ ጥሪ ተካፋይ ነው ብለዋል። ስለዚህ ይላሉ ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. ያቀረቡት ጥሪ ለክርስቶስ ታማኝ እንድንሆን የሚያሳስብ መሆኑ በማብራራት፣ ይህ ደግሞ ለክርስቶስ ያለን ታማኝነት የሚያረጋገጥ ክርስትያናዊ ኃላፊነት ነው ካሉ በኋላ፣ ወንጌላዊ ልኡክ እንደ ክርስቶስ እርሱን በመምሰል ወንጌል ለሁሉም ለማዳረስ የክርስቶስ ተከታይ እና ሓዋርያ መሆን ማለት ነው ብለዋል።

ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ረደምቶሪስ ሚሲዮ፣ በሚል ርእስ ሥር በደረስዋት አዋዲት መልእክት፣ የዚህ የልኡክነት መሠረት በማብራራት ተልእኮ በክርስትያኖች መካከል በሚደረገው የጋራው ውይይት አማካኝነት ጭምር የሚሸኝ መሆኑ በሥፋት በማስረዳት፣ የክርስቶስ ወንጌል እርሱም የድኅነት አዲስ መልእክት ለመላ ዓለም ማብሰር ለተለያዩ አቢያተ ክርስትያን የጋራው ውይይት የሚያነቃቃ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.