2010-02-01 13:26:48

ጸሎት ስለ ቅድስት መሬት


ትላንትና ሁለተኛ ዓለም አቀፍ ስለ ቅድስት መሬት የጸሎት ቀን ተከብሮ መዋሉ ሲገለጥ፣ ይህ ቀን በመላ ዓለም የሚኖሩት ክርስትያኖች የሚያስተባብር፣ በማስተባበር በዚህ ሀሳብ መሠረት ባንድነት ለመጸለይ የሚያነቃቃ RealAudioMP3 ዕለት መሆኑ በቅድስት መሬት የቅድስት መንበር ቅዱሳት ሥፍራ አስተዳዳሪ ኣባ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል። በቅድሚያ ለቅድስት መሬት የሚያስፈልገው ጸሎት ነው። ስለ ቅድስት መሬት መጸለይ እጅግ ያስፈልጋል፣ ባለፈው ዓመት ዕለቱን ምክንያት በማድረግ 800 የተለያዩ የክርስትያን ማኅበረሰብን ወክለው ለቅዱስ መሬት በአንድነት ለመጸለይ በቅድስት መሬት በሰባሰባቸውንም አስታውሰው፣ ዘንድሮ ቀኑን ምክንያት በማድረግ በቅድስት መሬት ለዚህ የጸሎት መርሃ ግብር የተገኙት በሺሕ የሚቆጠሩ ናቸው ብለዋል።

ቅድስት መሬትን ካለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለማሰብ ለመገመት አይቻለም፣ ስለዚህ ስለ ቅድስት መሬት መጸለይ ማለት ክርስቶስን መጸለይ ማለት መሆኑ አስረድተው፣ ክርስቶስን መጸለይ ደግሞ የክርስትያን ጸሎት ማእከል ማን መሆኑ እና ጸሎታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑ ያስረዳል ብለዋል። ክርስትያን ማኅበርሰብ ቅድስት መሬትን በማሰብ በኅብረት መጸለይ ማለት፣ የክርስትያኖች አንድነት ማነቃቃት መሆኑም ገልጠው፣ ጸሎት የስሜት ወይንም የግል የልብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የጋራም ጭምር ነው። ስለዚህ በጋራ መጸለይ እያንዳንዱ ለመተባበር እምነትን እግብር ላይ ለማዋል ያበረታታል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.