2010-02-01 13:25:47

የእግዚአብሔር አገልጋይ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ


ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ብፅእና እንዲታወጅላቸው መንፈሳዊው እና ሰብአዊው የላቀው ምግባር ብርታት በጥልቀት በማጥናት የሚከታተሉት ብፁዕ አቡነ ስላዎሚር ኦደር ከጋዜጠኛ ሳቨሪዮ ጋይታኖ ጋር በመሆን RealAudioMP3 የር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መንፈሳዊ እና ሰብአዊ የምግባር ብርታት የሚያስተነትን ለምን ቀዱስ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሓፍ በቅርቡ በይፋ መቅረቡ የሚታወስ ነው። ብፁዕ አቡነ ኦደር ስለ ጉዳይ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ የኖሩት ሕይወት ሰብአዊነት ሙላት ያጎላ፣ በእግዚአብሔር ፍቅር የተቃጠሉ፣ ለክህነት ጥሪያቸው የላቀ ፍቅር ያላቸው ሕይወታቸው ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው ሙሉ ፍቅር መሠረት የመሩ እና እራሳቸው ከዚህ ፍቅር ጋር ያመሳሰሉ ክርስቶስ በመምሰልም የተጉ ናቸው ብለዋል።

የእግዚአብሔር አገልጋይ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በተመስጦ ሕይወት የተካኑ ናቸው ካሉ በኋላ፣ በመንፈሳዊ ተመስጦ ሕይወት የተካኑ ነበሩ ሲባል ይላሉ ብፁዕ ኣቡነ ኦደር፣ ሰብአዊነታቸውን በሙላት የኖሩ ማለት መሆኑ አስረድተው፣ ዓለምን እና መላውን የአለም ሕዝብ በዚህ ሰብአዊነት በተካነው ዓይን የተመለከቱ፣ በታሪክ የእግዚአብሔር ኅልውና ጠልቀው የተገነዘቡ፣ የዚህ ሕላዌ ምልክቶችን ለይተው ለማንበብ የቻሉና ለሕዝብ ለማሳወቅ የተጉ ናቸው ብለዋል።

ግልጽነት የተካኑ በፊታቸው የእምነት ብርሃን የሚታይባቸው ከክርስቶስ ጋር የነበራቸው የጠለቀው እና ጥብቅ ግኑኝነት ካንደበታቸው ካቀራረባቸው በሚያካሂዱት ግኑኝነቶች በሚሰጡት አስትሰምህሮ ጎልቶ የታየ ነው። ምድራዊው ሕይወታቸውን የክርስቶስ ክህነት በመኖር በነበራቸው ጴጥሮሳዊ ሥልጣን እርሱን በዚህ ምድር ወክለው የኖሩ ናቸው። ለማርያም የነበራቸው የላቀው ፍቅር በመግለጥም ለሴቶች መብት እና ፈቃድ ክብር እና ማንነት መከበር ካለ መታከት ያስተማሩ የሴት ክብር ለይተው በጥልቀት የተረዱ እና ይኽ ጉዳይ በዓለም ደረጃ እንዲታወቅ ጥረት ያደረጉ መሆናቸው በመገልጥ፣ በመጨረሻ የእግዚአብሔር አገልጋይ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ምንም እንኳ የፖላንድ ተወላጅ ቢሆኑም አባትነታቸው ኵላዊነት መልክ ያለበሱ ናቸው ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.