2010-02-01 13:28:38

ኬንያ፣ በድኻ እና በሃብታም መካከል ያለው ልዩነት አሳሳቢነት


የተባበሩት መንግሥታት የከተማ መስፋፋት ጉዳይ የሚከታተል የከተሞች መስፋፋት ርእሰ ጉዳይ ያደረገ እ.ኤ.አ. መጋቢት ወር በብራዚህል ሪዮ ደ ጃኔሮ ከተማ ዓለም አቀፍ ጉባኤ መጥራቱ ከተባበሩት መንግሥታት የተሰራጨ ዜና RealAudioMP3 ሲያረጋገጥ፣ ይኸ ሊካሄድ የተወሰነው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ምክንያት በማድረግ የተባበሩት መንግሥታት የከተሞች ጉዳይ የሚከታተለው ጽ/ቤት በቅርቡ የኬንያው መንግሥት በአገሪቱ በድኻው እና በሃብታም መካከል ያለው ልዩነት በተመለከተ የሰጠው ጥናታዊ ሰነድ መሠረት በማድረግ እንዳሳወቀው፣ በኬንያ በናይሮቢ ሞምባሳ ኤሌዶረት እና ናኩሩ ከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጅ የሚተዳደረው ድኻው የአገሪቱ ዜጋ በብዛት የሚገኝባቸው ከተሞች መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ 10 በመቶ የአገሪቱ ዜጋ ከአገሪቱ መላው ሃብት ክፍል ውስጥ 44 በመቶ የሚቀጣጠር መሆኑ እና 10 በመቶ የሚገመተው የአገሪቱ ድኻው ሕዝብ ከአገሪቱ ሃብት ውስጥ 1 መቶኛውን ብቻ የሚቆጣጠር መሆኑ ሰነዱን የጠቀሰው ሚስና የዜና አገልግሎት ካሰራጨው ዜና ለምረዳት ተችለዋል።

በድኻው እና በሃብታሙ መካከል ያለው የኑሮ ልዩነት ከዕለት ወደ ዕለት እጅግ ከፍ እያለ ከሚታይባቸው አገሮች ውስጥ፣ ኬንያ ሁለተኛው ደረጃ ይዛ እንደምትገኝም ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.