2010-02-01 13:27:37

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ፣ በዓለም የተስፋ ምልክቶች ናችሁ


የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የወጣቶች ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚከታተለው ድርገት ባዘጋጀው የካቶሊክ የማኅበራዊ ትምህርት ሳምንት ምክንያት በማድረግ፣ የመላ የሊጉሪያ ካቶሊክ ወጣቶች ባካሄዱት ስብሰባ ተገኝተው RealAudioMP3 ስብሰባውን ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ባሰሙት ስብከት ካቶሊክ ወጣት በዚህ በምንኖርበት ዓለም የተስፋ ምልክት መሆን አለበት ብለዋል።

ዘንድሮ የመላ ኢጣሊያ የካቶሊክ ማህበራዊ ትምህርት ሳምንት እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 14 ቀን እስከ ጥቅምት 17 ቀን በሬጆ ካላብሪያ የኢጣሊያ ወጣቶች በዛሬይቱ ኢጣሊያ በሚል ርእስ ተመርቶ እንደሚካሄድ የኢጣሊያ የወጣቶች ግብረ ኖልዎ ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ ባሰሙት ስብከት፣ ክርስቶስን እንመልከት ቃሉን ልብ እንበል የቤተ ክርስትያንን ቃል እናዳምጥ የቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርትን እንገንዘብ እንከተል በማለት በክርስቶስ እና በቤተ ክርስትያን መካከል የቀጣይነት ግኑኝነት እንዳለ አስረድተው፣ ለሕዝብ በተለይ ደግሞ ለተናቁት በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙት ቅርብ በመሆን የሚመሰከር ግኑኝነት ነው። ስለዚህ እያንዳንዱ ወጣት በሚኖረው ጥሪ የዚህ እውነተኛ አገልግሎት ተሳታፊ መሆን ይገባዋል ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ በመጨረሻ ሁሉም በአዲስ መንፈስ በታደሰ እምነት አማካኝነት ለቅድስና መጠራቱ በማወቅ በዚህ በምንኖርበት ዓለም የተስፋ ምልክት መሆን ይግባዋል እንዳሉም ለማወቅ ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.