2010-01-29 14:13:58

የሕይወት ፍጻሜ


ሮማ በሚገኘው የካቶሊክ መንበር ጥበብ ትላንትና የሕይወት ፍጻሜ በሚል ርእስ ሥር ሰፊ አውደ ጥናት መካሄዱ ተገለጠ። በዚህ በተካሄደው ዓውደ ጥናት የሰብአዊ ክብር እና የሕይወት መሠረታዊ እሰይታ ዳግም ተበክረዋል። RealAudioMP3 የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. እፊታችን የካቲት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ የሕይወት ቀን እንዲታሰብ የሰጠው መገልጫ መሠረት በማድረግ የተከናወነ አውደ ጥናት መሆኑ ሲገለጥ፣ በቅድሚያ ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት እንዲጠበቅ ያሳሰበው የትላንትናው ጉባኤ፣ ገና መድኃኒት ባልተገኘለት በሽታ ቢለከፍም መድኃኒት አልተገኘለትም ብሎ ጸረ ባህርያዊ በሆነው መንገድ ለሞት መዳረግ ጸረ ሕይወት ነው።

የካቶሊክ መንበረ ጥበብ የሕክምና ክፍል የቀዶ ጥገና ሕክምና የስነ ማደንዘዣ መድኃኒት እና ከገዶ ጥገና ሕክምና ቀጥሎ የሚሰጠው የስነ ሕክምና ድጋፍ መምህር ፕሮፈሰር ሮዶልፎ ፕሮየቲ ስለ ተካሄደው አውደ ጥናት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ከበሽታ ዝግመት የሚያጋጥም ሞት እና በቀጥታ በሽታው ለመፈወስ ወይንም ለሞት እንዳያደርስ የሚሰጠው የሕክምና ስልት እንዲቋረጥ በማድረግ የሚከሰት ሞት መለየት አስፈላጊ ነው። ስለዚህ አንድ ታማሚ ወይንም መድኃኒት ገና ባልተገኘለት በሽታ ለታመመው ሰው የሚሰጠው የሕክምና ድጋፍ እንዲቋረጥ ማድረግ የሞት ፍርድ ነው በዚህ ውሳኔ የሚረጋገጠው ሞት ከበሽታው ዝግመት አንጻር የሚረጋገጥ የሞት አይነት አይደለም፣ ስለዚህ ስቃይ የለሽ ሞት ውሳኔ ነው ብለዋል።

የተካሄደው አውደ ጥናት ስለ ሕይወት ፍጻሜ ርእስ በማድረግ ተወያይተዋል፣ ማንም ገና መድኃኒት ባልተገኘለው በሽታ ማቆ ሕሊናው ስቶ የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ቢቀርም፣ ባህርያዊ ሞቱን መጠባበቅ እንጂ በሕክምና መሣሪያ የሚሰጠው ድጋፍ ይቋረጥ ብሎ በመጠየቅ ለሞት መፍረድ አይቻልም። ታማሚው ባንድ ወቅት ገና ሳይታመም ሕሊናዮን የሚያስት በሽታ ያጋጠመኝ እንዲሆን ስቃይ የለሽ ሞት ይሰጥኝ ብሎ ቃለ ኑዛዜ የሰጠ ቢሆንም፣ ሕሊና ስቶ ያልጋ ቁራኛ መሆን በተመለከተ ቀጥተኛ ልምድ ስለ ሌለው የሰጠው የኑዛዜ ቃል ተቀባይነት የለውም። ሓኪም ከበሽታ የሚፈውስ እንጂ በጠና የታመመው እና መድኃኒት ባልተገኘለት በሽታ የተለከፈ ሕሊናውን በሳተ ላይ የሞት ፍርድ ለመበየን የተመደበ አይደለም ካሉ በኋላ ይህ ሃሳብ አውደ ጥናቱ ጠለቅ በማድረግ እንደተወያየበት ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.