2010-01-29 14:17:18

ሃይቲ፣ የሕጻናት ጉዳይ አሳሳቢነት


በሃይቲ በተከሰተው ርእደ መሬት ሳቢያ ወላጅ አልባ የቀሩት ከርእደ መሬቱ ክስተት በፊት በተለያዩ ምክንያት በወላጅ አልባ መጠለያ ማእከል ይገኙ የነበሩት ሕጻናት ርእደ መሬቱ ባስከተለው አደጋ ለሞት ተጋልጠው RealAudioMP3 የተረፉት እና በተከሰተው ግርግር እና ሥርዓት አልቦነት ምክንያት በተለያዩ የወንጀል ቡድኖች እየታደኑ ለሕገ ወጥ ዝውውር አደጋ መጋለጣቸው እንዲሁም የሞት አደጋ የደረሰባቸው ጠያቂ የሌላቸው ባንድ ላይ አጉሮ አፈር አዳም የማልበሱ ተግባር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመግለጥ ሥጋቱን ገሃድ አድርገዋል።

ወላጅ አልባ የሆኑትን ሕጻናት ባሳዳጊነት ለመረከብ የሚደረገው ሕጋዊ አሠራር ቀርቶ ሕጻናቱን እንደ ወላጅ ለማሳደግ የሚሹት ጭምር አጋጣሚውን በመጠቀም አለ ፈቃድ እና ሕግ፣ ሕጻናቱን በቀጥታ ከወንጀል ቡድኖች እጅ የመረከቡ ሕገ ወጥ አሠራር እየተከተሉ መሆናቸው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት አስከባሪ የበላይ ድርጅት ተጠሪ ናቪ ፒላይ በመጥቀስ ጉዳይ በጄነቭ ለተካሄደው የድርጅቱ ክፍለ ስብሰባ ባስተላለፉት መልእክት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.