2010-01-27 12:49:14

ብራዚል፣ ሳን ፓውሎ አገረ ስብከት አንደኛ የዓለማውያን ምእመን ጉባኤ


በላቲን ሥርዓት እ.ኤ.አ. ጥር 25 ቀን በየዓመቱ ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለበት ዕለት ክብረ በዓል መሆኑ ሲታወቅ፣ ይህ ዓቢይ በዓል በብራዚል ሳን ፓውሎ ከተማ ለየት ባለ መልኩ ቅዱስ ጳውሎስ የዚህች RealAudioMP3 ከተማ ጠባቂ በመሆኑም ጭምር እጅግ ደምቆ የሚከበርባት ከተም ነች። የከተማይቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ኦዲሎ ሸረር በዓሉ ምክንያት በማድረግ በቅዱስ ፓውሎስ ባሲሊካ ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት፣ ዕለቱ የከተማይቱ የዓለማውያን ምእመናን አንደኛው ጉባኤ በይፋ የሚከፈትበት መሆኑ በመግለጥ፣ ዓለማውያን ምእመናን ታድሰው ቤተ ክርስትያናቸውን ለማደስ በመትጋት ስለ ተለያዩ ጥሪዎች የሚያስተነትኑበት እና እንዲሁም የቤተ ክርስትያን የሥልጣን ትምህርት በቲዮሎግያው በቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት መሠረት ዓለማዊ ምእመን ሲባል ምን ማለት መሆኑ በጥልቀት የሚያስነትኑበት እና ስለ ጉዳዩ ትኵረት የሰጠ አስተምህሮ የሚቀበሉበት እንደሚሆን ገልጠዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ኦዲሎ ሸረር በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የአሕዛብ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ክብረ በዓል ምክንያት፣ በእሳቸው እረኝነት ሥር የሚመራው ሰበካ አንደኛ የአለማውያን ምእመናን ጉባኤ ለማካሄድ የወሰነበት ምክንያት፣ ሚሥጢረ ጥምቀት የተቀበለ ሁሉ የዚህ ጸጋ ጥልቅ ግንዛቤ ኑሮት፣ የክርስትያን ምእመን የክርስቶስ ተከታይ ከመሆኑ ዘንድ የመነጨው ክብር ዳግም የሚያረጋግጥበት ሚሥጢረ ጥምቀት በመቀበል ክርስትያን መሆን ምን ማለት መሆኑ የሚያስተነትንበት ጉባኤ ነው ብለዋል። ይህ የቫቲካን ሁለተኛው ጉባኤ የመላ ላቲን አሜሪካ እና ካራይቢ አምስተኛው የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሰነድ ጭምር ስለ ዓለማውያን ምእመናን ያስተላለፈው ውሳኔ በማጤን ስለ መለያው ስለ ክርስትያናዊ ክብር የሕይወት ባህል እና በቤተ ክርስትያን የዓለማውያን ምእመን ተልእኮ በተመለከተ በማስተንተን ጥልቅ ትምህርት የሚቀስምበት ጉባኤ እንደሚሆንም አረጋግጠዋል።

ይህ አንደኛው ጉባኤ ቀጣይ የሆነ ሁለት ምዕራፎች እንደሚኖረው በማሳወቅም እያንዳንዱ ምእመን ባለው ልዩ ሙያ እና ችሎታ በማደራጀት በተለያዩ የቤተ ክርስትያን ዘርፎች በማሳተፍ የሚሰጠው አገልግሎት በተመለከተ የሚስተነተንበት እርሱም እ.ኤ.አ. ሐምሌ እና ነሓሴ የሚከናወን ሲሆን፣ በመጨረሻም በዚህ 2010 ዓ.ም. ማብቅያ የክርስትያን ምእመን አስተዋጽኦ ለከተማይቱ እና ለማኅበረሰብ በሚል ርእስ የተመራ እቅድ መሠረት በማድረግ ጥልቅ ጥናታ እንደሚደረግ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.