2010-01-25 15:16:01

የክርስትያኖች አንድነት የጸሎት ሳምንት


በየዓመቱ ስለ ክርስትያኖች አንድነት የሚደረገው የጸሎት ሳምንት ነገ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የቅዱስ ጳውሎስ መለወጥ በምታስታውስበት በዓል ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ RealAudioMP3 መሪነት ሮማ ፎሪ ለ ሙራ በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ባሲሊካ በሚቀርበው ሁለተኛው የሠርክ ጸሎት አማካኝነት እንደሚፈጸም ተገልጠዋል።

ዕለቱ ምክንያት በማድረግ የቅዱስ በርናርዲኖ የክርስትያኖች አንድነት የጥናት ተቋም ሊቀ መንበር አባ ሮበርቶ ጂራልዶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄድቱ ቃለ ምልልስ ባለፉት የመጨረሻ ዓመታት ስለ ክርስትያኖች አንድነት የሚደረገው ጥረት አበይት ውጤቶች እንዳስጨበጠ በመግለጥ፣ በተለይ በተለያዩት አቢያተ ክርስትያን መካከል መቀራረብ እና የጋራ አመለካከት ለማረጋገጥም ማስቻሉንም በማስታወስ የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካተርበርይ ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊሊያምስ ስለ ቤተ ክርስትያን ባህርይ በተመለከተ የተደረሰው መግባባት የሚደነቅ ነው ብለዋል።

የክርስትያኖች አንድነት የሚመለከተው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ቫልተር ካስፐር ከተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ጋር የሚደረገው የጋራው ውይይት በአቢያተ ክርስትያን መካከል ያለው ልዩነት ለይቶ ለማወቅ እንደሚያግዝ እና ይኽ ደግሞ አንድነት ለማረጋገጥ ለሚደረገው ለጋራው ጥረት መሠረት ነው በማለት የሰጡት አስተያየት አባ ጂራልዶ በማስታወስ፣ ለአንድነት የሚደረገው ጥረት ተስፈኛ ነው ብለዋል።

አቢያተ ክርስትያን የመጀመሪያ የቤተክርስትያን ጉባኤዎች ስለ ቅድስት ሥላሴ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተመለከተ ያጸደቁዋቸው አንቀጸ ሃይማኖቶች የሚቀበሉ መሆናቸው ጠቅሰው፣ ከዚህ ቀጥለው የታዩት ልዩነቶች የሚያንጸባርቁዋቸው እሴቶች በተለያየ አቅጣጫ መመልከት እንደሚቻል ገልጠው፣ ልዩነት ሃብት ሊሆን እንደሚችል መዘንጋት የለበትም ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.