2010-01-25 13:40:09

የካቶሊክ የመገናኛ ብዙኃን እና የመገናኛ ብዙሃን ሠራተኞች እና ጋዜጠኞች ጠባቂ ቅዱስ


የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ትላትና በላቲን ሥርዓት የካቶሊክ ጋዜጠኖች እና የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች ጠባቂ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዲ ሳለስ በዓል RealAudioMP3 ምክንያት ለኢጣሊያ የራይ ጋዜጠኞች እና ሠራተኞች የቀረበው መስዋዕተ ቅዳሴ በመምራት ባሰሙት ስብከት፣ ብፁዕነታቸው ባለፈው ዓመት ማብቂያ የንጽሕት ድንግል ማርያም በዓል ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሰው ልጅ ለማነጽ ለመገንባት የሚገፋፋው ውስጣዊው ፍላጎት ችላ እንዳይል በማለት ያቀረቡት ጥሪ በማስታወስ ሁሉም በአካባቢው በሚሆነው ጉዳይ ብቻ ሳይታጠር ለመተባበር ንቁ መሆን እንዳለበት እና በዚህ ጉዳይ የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች እና ጋዜጠኞች ያላቸው ኃላፊነት አቢይ መሆኑ ማብራራታቸው ተገልጠዋል።

ጋዜጠኝነት በጠቅላላ የመገናኛ ብዙኃን በእውነት ላይ የተመሠረተ እውነት የሚያንጸባርቅ እንጂ ወገነና ወይንም ወይንም የንግዱ ዓለም ውሳኔ እና መመሪያ ብቻ ከመከተል አደጋ በራቅ አለበት ካሉ በኋላ የማየገናኝ ለውጥረተ የሚገፋፋ መሣሪያ መሆን የለበትም ብለዋል። በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመጥቀስ የዜና እና የመገናኛ አውታሮች ለተመሠረቱበት ቅዱስ አላማ ታማኝ መሆን አለባቸው እንዳሉም ለማወቅ ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.