2010-01-25 15:18:43

ዓለም አቅፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን


ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚከበረው 44ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ምክንያት ክህነት እና ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ በዚህ በአኃዝ ቀመራ ሳይንስ እጅግ RealAudioMP3 በተራቀቀበት ዘመን በሚል ርእስ ሥር የሚያስተላለፉት መልእክት ትላትና በቫቲካን የማስታወቂያ እና የማኅተም ክፍል አማካኝነስት የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ቤተ ክርስትያን የካቶሊክ የመገናኛ ብዙኃን ጠባቂ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዲ ሳለስ በምታስታውስበት ዕለት ዋዜማ ይፋ መቅረቡ ተረጋገጠ።

ይህ ዘንድሮ በመከበር ላይ ያለው የክህነት ዓመት አቢይ ግምት የሰጠ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያስተላለፉት መልእክት ክህነት እና ስብከተ ወንጌል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በአኃዝ የቅመራ ሥልት የሠለጠነው የመገናኛ መሣሪያ ችላ ሊለው አይገባም እንዳውም የዚህ መሣሪያ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባው ማሳሰባቸው ሲነገር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በሁሉም ዘንድ እንዲታወቅ ልኡካነ ወንጌል ከዚህ አዲሱ የመገናኛ ብዙኃን መሣሪያ ጋር ሊተዋወቁ እና ተገቢ እውቀት ሊኖራቸው ይገባል፣ ስብከተ ወንጌል ወቅታዊ ሁኔታ የሚያነብ መሆን እንደሚገባው የሚያሳስብ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።

እጅግ ፈጣን በሆነው አካሄድ እየተረጋገጠ ያለው ሥልጣኔ በቅርብ የሚነካው ወጣቱ የህብረተ ሰብ ክፍል መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመጥቀስ፣ ቤተ ክርስትያን ካህናት ልኡካነ ወንጌል ለነዚህ የኅብረተ ሰብ ክፍል ለየት ባለ መልኩ ትኵረት ሊስጡ እንደሚገባም ማሳሰባቸው ከቫቲካን የማስታወቂያን እና የማኅተም ክፍል የተሰጠው መግለጫ ያረጋገጣል።

የክህነት ሚስጢር ከክርስቶስ ጋር በግል ከመገናኘት እና ከጥልቅ ጸሎት የመነጨ ጥሪ መሆን እንዳለበት ቅዱሱነታቸው በማስረዳት ወንጌል በማብሰር ቅዱሳት ሚስጢራትን በመሥራት በቃል እና በህይወት የሚመሰክር መሆን አለበት እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.