2010-01-25 13:37:39

ሲመተ ጵጵስና


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶቤ በቦዝኒይ ኤርዘጎቪና በሚገኘው ካቴድራል በክዋይት በባህረይን እና በቃታር የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል እንዲሆኑ ለተሸሙት ለአባ ፐታር ራጂች RealAudioMP3 የጵጵስና ማዕርግ ሰጡ።

ብፁዕ ካርዲናል በርቶኔ የጵጵስና ማዕርግ ለመስጠት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፣ ውይይት፣ በመቀራረብ በመተዋወቅ በሰብአዊ በሃይማኖታዊ ረገድ የሚገለጥ፣ መሆን እንዳለበት በማብራራት፣ ለኚህ አዲስ የቅድት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል እንዲሆኑ ተመርጠው የጵጵስና ማዕረግ ለተሰጣቸው ብፁዕ አቡነ ራጂች በዚህ በተሰጣቸው አዲስ ኃላፊነት በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ ተሸኝተው ቤተ ክርስትያን እንዲያገለግሉ ጸልየዋል። ከቅዳሴው ሥነ ሥርዓት በኋላ በቀረበው የምሳ ግብዣ ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ ባሰሙት ንግግር፣ ጳጳስ ለቤተ ክርስትያን ለቤተ ክርስትያን ባህል ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ታማኝ እና ታዛዥ በመሆን የቤተ ክርስትያን አንድነት መስካሪ ነው በማለት፣ የባህል የጎሳ ልዩነት የማይመለከት በማኅበረሰብ ዘንድ የወንጌል አንድነት አብሳሪ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.