2010-01-22 16:33:05

የክርስትያን ኅብረት ጸሎተ ሳምንት


ባለፈው ሰኞ የጀመረው የክርስትያን ኅብረት ጸሎተ ሳምንት እየቀጠለ ነው።

የትናንትና አስተንትኖ በእምነት ምስክርነት አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ ነበር።

ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በብዙ ጉዳዮች የምትተባበር ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን አስመልክተው የክርስትያን ኅብረትን የሚያራምድ ጳጳሳዊ ምክር ቤት አባል የሆኑ አባ ሚላን ዙስት የሚከተለውን ማብራርያ ለቫቲካን ረድዮ ሰጥተዋል።

ኦርቶዶክሳውያን በጸሎት ሥርዓተ አምልኮአቸው ስለ ቤተ ክርስትያን አንድነት ይጸልያሉ፣ ከዚህም በላይ ለክርስትያን ኅብረት በተዘጋጀው ጸሎተ ሳምንት ሁል ጊዜ ይሳተፋሉ አንዳንዴም ፕሮግራሙን የሚያዘጋጁትና የሚያካሄዱት እሳቸው ናቸው። ለምሳሌ በሩማንያ ጸሎተ ሳምንቱ ከሌሎች ማኅበረ ክርስትያን ጋር በመወያየት ይዘጋጃል፣ እንዲሁም በአንዳንድ የመሀከለኛ ምሥራቅ አገሮች እንደዛ ይደርጋል። ከኦርቶዶክስ ጋር የሚደረገው ትብብር ከሌሎች አብያተ ክርስትያንና ማኅበረ ክርስትያን ለየት ያለ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። በአጠቃላይ የተመለከትን እንደሆነ ሌሎች እንደታዛቢዎች እንጂ በጸሎቱ ተካፋዮች ሊሆኑ አይችሉም፣ ይህ ለምእመናናችን ሊያገርማቸው ይችላል፣ ነገር ግን በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያንም ከሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ በፊት እንደዛ ነበር፣ ኦርቶዶክሳውያን ይህንን የመሰለ ጉባኤ ገና ስላላካሄዱ እስካሁን በሚያደርጉት ጥረት ሊመሰገኑ ይገባል። ሲሉ ያለንን ግኑኝነት ካብራሩ በኋላ የቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ከአንድ ዓመት በፊት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል የሞስኮ ፓትርያርክ ሆነ መመረጥ የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ለሌሎች አብያተ ክርስትያን የትብብር በር ይከፍታል የሚል ተስፋ ተጥሎበት ነበር፣ በዚሁ ምርጫ የተለወጡ ነገሮች አሉን” የሚል ነበር። መልሳቸውም “በሁለቱም ወገኖች በተደረገው ጥረት በተለይም በሩስያም በምዕራቡ አብያተ ክርስትያን በተለያዩ ደረጃዎች የተደረጉ ውይይቶች እያደጉ ስለሆነ፣ ከሩስያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ያለው ግኑኝነት እየተሻሻለ መጥተዋል፣ በአንጻሩም በኡክራይን የቤተ ክርስትያኑ ሁኔታ ገና ውስብስብ ነው፣ ቢሆንም ቅሉ እዛ ላይም ዕድገት ይታያል ያለው ችግርም በጊዜ እንደሚፈቱ ባለተስፋዎች ነን። በቅርብ ጊዜ ውስጥ የቍስጥንጥንያ ኢኩመኒካዊ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ በርጠለሜዎስ 1ኛ ሞስኮን ይጎበኛሉ፣ ይህ ጥሩ ግኑኝነት ለአንዳንድ ችግሮች መፍትሔ ሊያስገኝ ይችላል ብለን እናምናለን፣ ይህ ግኑኝነት በካቶሊካዊትና በኦርቶዶክሳዊት አብያተ ክርስትያን ያለውን ግኑኝነት ሊያሻሽል ነው። እንደ ተጨባጭ ምሳሌ የሞስኮ መንበረ ፓትርያርክ የውይይት ልኡካን እአአ በ2007 ዓ.ም ራቨና ላይ ከመንበረ ቍስጥንጥንያ በተከሰተው አለመግባባት ከድርድሩ አቋርጠው ኖሮ አሁን ግን እንደግና ወደ ውይይት ጠረጴዛ መመለሳቸው ለኅብረቱ ተስፋ የሚሰጥ ነው፣ ሲሉ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያንና በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ስለሚካሄደው የኅብረት አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.