2010-01-18 16:15:48

ሃዪቲ እና የመሬት ነውጥ ፡


ባለፈው ማኽሰኛ በካራይቢ ሃዪቲ መሬት ተናውጦ ፡ በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ይታውቃል

በዚሁ አደጋ ሕይወቱ ያጣ ህዝብ በውል የሚታወቅ ባይሆንም፡ የሀገሪቱ ባለሥልጥናት ከአንድ መቶሺ በላይ መሞቱ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ሰብአውያን ድርጅቶች በዚሁ የመሬት መናወጥ አደጋ ከሃምሳ ሺ በላይ ህዝብ ሕይወቱ እንዳጣ ነው የሚያመለክቱት ።

በሪኽተር ሰባት የተለካው የመሬት ነውጡ ርእሰ ከተማ ፖርት አው ፕሪንስን በኃል መጐዳትዋ በተለይ ግን ድሃው ሕብረተሰብ የሚኖርበት አከባቢ ማውደሙ ለማወቅ ተችለዋል ።

በየሃዪቲ ርእሰ ከተማ ፖርት አው ፕሪስ አንድ ሚልዮን ህዝብ እንደሚኖር ይታወሳል።

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከዓለም ሀገራት በእጅጉ የደሄየች ሃዪቲ ደሴት ተፈጥሮአዊ መቅሰፍት ተጨምሮበት ሁኔታዋ ከነበረው የከፋ እንዲሆን እንዳደረገው ታውቆዋል።

በአጠቃላይ የዓለም ሀገራት መንግስታት ለጋሽ ድርጅቶች ሰብአውያን ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የመሬት ነውጡ እንደተሰማ ግዙፍ ርዳታ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸው በመግለጽ አፋጣኝ ርዳታ በመላክ ላይ መሆናቸው ይመከታል።

ከዓለም አቀፍ ወደ ደሴትዋ የሚጐርፈው ግዙፍ ርዳታ የሚያቀንብር መንግስት ይሁን አገሮች አቀፍ ድርጅት ባለመኖሩ በዚሁ ረገድ ኃይለኛ ችግር መከሰቱ እየታየ ነው ።

የሃዪቲ ደሴት መንግስት ከዓለም አቀፍ ሀገራት እና ሰብአውያን ድርጅቶች ሀገሪቱ ውስጥ የሚገባ ርዳታ ለማቀናበር እና ለህዝብ ማከፋፈል ዓቅም ስለ ሌለው ከመሬት ነውጡ አርባ ስማንት ሰዓታት በኃላ ለኃይለኛ ችግር የተዳረገው ህዝብ ርዳታ ገና ርዳታ እንዳልደረሰው

ተመልክተዋል ።

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት መሪዎች ጂዮርጅ ዳብልዩ ቡሽ እና ቢል ክሊንተን ለደሴት ሃዪቲ የምሰጠ ዓለም አቀፍ ርዳታ በማቀናበር እና በማስተባበር መሪነት እንዲሰሩ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ መጠየቃቸው እና ጥያቅያቸው መልስ ማግኘቱ የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ሮበርት ጊብስ አስትታውቀዋል።

ርዳታ በመዘግየቱ ከጥፋት የዳነው ህዝብ የሞቱት ሰዎች አስከሬኖች አጉረው ገደናዎች ሲዘጉ ተስተውለዋል ። የፖርት ኦው ፕሪንስ አውሮፕላን ማረፊያ የርዳታ አውሮፕላኖች ማስተናገድ እንዳልቻለ ተስተውለዋል ፡ ርዳታ የጫኑ አውሮፕላኖች ተጓራባች ወደ ሆነችው ሳን ዶሚንጎ እንዲዘዋወሩ መደረጋቸው ተመልክተዋል።

የሃዪቲ ደሴት ፕረሲዳንት ረነ ፕረቫል ተፈጥሮአዊ መቅሰፍቱ ባደርሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጠው ከሚኖሩበት ለመውጣት እንደተገደዱ እና የሚተኙበት እያፈላልለጉ መሆናቸው መግለጻቸው ተገልጸዋል ።

እንዲህ ዓይነቱ ተፈጥሮአዊ መስፍት ሲያጋጥም ከተለያዩ ክፍለ ዓለሞች የሚደርሱ ርዳታዎች የሚስተናብር የማቀናበር እና የማከፋአል ልምድ ያለው ዓለም አቀፋዊ አካል እንደሚያሻ የደሴት ሃዪቲ ሁኔታ ያመለክታል።

ወደ ሰብአዊ ርዳታ ሁኔታ እንመለስ እና ባለፈው ማክሰኞ በደሴት ሃዪቲ መሬት ተንቀጥቅጦ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ እንደተሰማ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ሮብአዊ እስተምህሮ በሰጡበት ግዜ የዓለም መንግስታት እና ሰብአውያን ድርጅቶች ፡ ለከባድ ችግር የተጋለጠ የደሴት ሃዪቲ ህዝብ አፋታኝ ርዳታ እንዲሰጡ መማጸናቸው ይታወሳል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሮማዊት ቤተክርስትያን በየርዳታ ተቋሞችው በኩል ለሃዪቲ ህዝብ አፋጣን ርዳታ እንደምትልክ ጠቅሰው ምእመናን ከሳቸው ጋር አብረው በአደጋው ስለሞቱት ሰዎች እንዲጠልዩ ጠይቀዋል።

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አደራ ተንተርሰው ኮር ኡኑም ተባለ የቫቲካን የተዋሀደ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ከየአመሪካ ካቶሊካዊ የርዳታ አገልግሎት እና ከሌሎች ሰብአውያን ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለሃዪቲ የገንዘብ እና የሰው ኃይል መላካቸው የጣልያን ካሪታስም እንዲሁ ለደሴቲቱ የምግብ እና መድኅኒት ርዳታ መላክዋ ታውቆዋል ።

ከስልሳ በላይ ካቶልካውያን ሰብአውያን ድርጅቶች ያቀፈ ካሪታስ ኢንተርናጽዮናሊስም በሊቀመንበር በብፁዕ ካርዲናል ኦስካር ሮድሪገጽ ማራዲያጋ መሪነት በደሴት ሃዪቲ በዘላቂ ርዳታ ለመሰማራት ወደ ቦታው ማቅናታቸው ተመልክተዋል።



የሮማ ሀገረ ስብከት አንድ መቶ ሺ ኤውሮ ለሃዪቲ መላኩ የጣልያን መንግስትም የሕክምና እና ምግብ ርዳታ የጫኑ ሁለት አውሮፕላኖች ከመላኩ ባሽገር የሲቪል ጥበቃ ተቋም ጠበብት ባለሙያዎች መላኩ አስታውቀዋል።

የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት በዚሁ የተያዝነው ጥር ወር ሃያ አራት ቀን በጠቅላላ የሀገሪቱ አብያተክርስትያናት ለሃዪቲ የገንዘብ መውጮ ለማደረግ ማቀዱ የረኪበ ጳጳሳቱ ቃል አቀባይ አስታውቀዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የፖርት ኦው ፕሪንስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚዮት እና በርካታ የሀገሪቱ ቤተ ክህነት አባላት በነውጡ ሳቢያ ሕይወታቸው እንዳለፈ ተያይዞ ተገልጠዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙንግ ድርጅቱ ለሃዪቲ ደሴት አስር ሚልዮን ዶላ ዝግጁ ማድረጋቸው ጠቁመው ፡ የዓለም ማኅበረሰብ የርዳታ እጁ እንዲዘረጋ ተማጥነዋል።

ደሴት ሃዪቲ በድኅነትዋ ላይ የፖሊቲካ መረጋጋት እንደሌላት የሚታወስ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አክባሪዎች ደሴቲቱ ላይ ሰላም እየከበሩ ሲሆን ፡ የዚሁ የሰላም አክባሪ ቡድን ዋና ሐላፊ ሐዲ ሃናቢ እና ምክትላቸው ሉዊስ ካርሎስ ዳ ኮስታ በመሬት ነውጥ ሳቢያ ጨምሮ አስራ ስድት ሰላም አክባሪዎች የአደጋው ሰላባ መሆናቸው ተመልክተዋል።

የብራዚል መንግስት መከላከያ ሚኒስትር ነልሶን ጆቢም በደሴት ሃዪቲ በሰላም ተልእኮ የነበሩ አስራ አራት ወታደሮች እና ሶስት ስቪሎች የብራዚል ዜጎች በዚሁ ተፈጥሮአዊ መቅሰትፍ ለሕለፈት መዳረጋቸው አስታወቁ ።

በፖርት አው ፕሪንስ ክሪስቶፈር በተባለ ሆቴል ውስጥ ከነበሩ ሁለት መቶ ሰዎች በሕይወቱ የወጣ ሰው እንዳልነበረ ከቦታው የመጣ ዜና ያመልክታል።

ይህ በዚህ እንዳለ በዚሁ አደጋ በሆቴሎች ህንጻዎች እና መኖርያ ቤቶች ተደፍነው ለበርካታ ሰዓታት የቆዩ ሰዎች እምብዛም አይደሉም እንጂ በሕይወታቸው እንደተገኙ ከቦታው የደርሱ ዜናዎች ያስገነዝባሉ።

የUs አመሪካ መሪ ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ የርዳታ አውሮፕላኖች መርከቦች እና ሆሊኮፕተሮች ወደ ሃዪቲ መላካቸው እና መንግስታቸው አንድ መቶ ሚልዮን ዶላር ለአፋጣን ርዳታ ዝግጁ ማድረጉ ዋሺንግቶን ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።የሩስያ ፌደረሽን የፈረንሳ እና የጃፓን መንግስታት ተመሳሳይ ርምጃ መውሰዳቸው ተገልጠዋል።

የፈረንሳ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብ አርናርድ ኩሽነር ሃዪቲ ውስጥ ከነበሩ አንድ ሺ ሶስት መቶ የፈረንሳ ዜጎች ዘጠና ስድስት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ጠቅሰው ፊታችን መጋቢት ወር በመሬት መናወጥ ሳቢያ ለፈራረሰችው ሃዪቲ ዳግመ ግንባታ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ለማከናወን እየታቀደ መሆኑ ተያይዞ አመልክተዋል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለሁለት ሚልዮን የሃዪቲ ህዝብን ዕለታዊ ምግብ ለማረብ በዝግጅት ላይ መሆኑ ሮም ውስጥ የሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ ካወጣው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከሌሎች የግብረ ሰናይ እና ለጋሽ ሀገራት ጋር በመተባበር የመሬት መናወጥ ለሆነ ህዝብ ዘላቂ ርዳታ ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑ አያይዞ አስታወዋል።

በደሴት በሃዪቲ ዳግም መሬት ይንቀጠቀጣል የተሚለውን ስጋት እንዳልተወገደ የሥነ መሬት ጠበብት ማመልከታቸ አከፖርት ኦው ፕሪንስ የመጣ ዜና ገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.