2010-01-13 17:03:40

የር.ሊ.ጳ. ጉባኤ አስተምህሮ 13.01.2010


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ የተለመደውን አጠቃላይ ሳምንታዊው የዕለተ ሮቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መክፈቻ ጸሎት አሳርገው ከመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 40 ከቍ.1-8 “እግዚአብሔር እንዲረዳኝ በትዕግሥት ተጠባበቅሁት። እርሱም ጩኽቴን ሰምቶ ልመናዬን ተቀበለኝ። ከአደገኛ ጕድጓድና ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ በአለትም ላይ በደህና አቆመኝ፥ ጉዳት እንዳይደርስብኝም አደረገ። አዲስ መዝሙር ስላስተማረኝ የምስጋና መዝሙር ለአምላካችን አቀርባለሁ፤ ይህን በማየት ብዙ ሰዎች ይፈራሉ፥ በእግዚአብሔርም ይታመናሉ። በእግዚአብሔር ብቻ የሚታመኑ ወደ ጣዕቶች የማይመለሱ ሐሰተኞች አማልክትን ከሚከተሉ ከዓመጸኞች ሰዎች ጋር የማይተባበሩ፣ የተባረኩ ናቸው። እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፥ ብዙ አስደናቂ ነገሮች አድርገህልናል፣ ከአንተ የሚወዳደር ማንም የለም፣ አንተ ለእኛ ያቀድህልንን መልካም ነገር ማንም ሊቆጥረው አይችልም። እኔ ስለእነርሱ ብዝርዝር ለመናገርና ለማውራት ብሞክር፣ ቍጥራቸው እጅግ የበዛ ይሆንብኛል። አንተ መሥዋዕትንና መባን አትፈልግም፤ እንስሳት በመሠውያ ላይ እንዲቃጠሉ ወይም ለኃጢአት ሥርየት የሚሆን መሥዋዕት እንዲቀርብልህ አትጠይቅም፣ በዚህ ፈንታ የአንተን ትእዛዝ በመስማት እንዳገለግልህ አድረግኸኝ። ስለዚህ “ስለ እኔ በሕግ መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት እነሆ እኔ መጥቻለሁ። አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ማድረግ በጣም እወዳለሁ፥ ሕግህንም በልቤ አኖራለሁ” አልሁ።” የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር በኤውሮጳ ዋና ዋና ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ትምህርተ ክርስቶስ አስተምረዋል። “ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ የመሀከለኛው ዘመን የክርስትና ትምህርት በምናጠናበት የዛሬ ትምህርታችን በሁለት ትላልቅ መነኮሳን የተካሄደው የቤተ ክርስትያን ተሓድሶን እንመለከታለን። በቤተ ክርስትያን ታሪክ በማንኛውም ጊዜ እውነተኛ የተሓድሶ አራማጆች ቅዱሳን ናቸው። በአሥራ ሦስተኛው ክፍለዘመን ቅዱስ ፍራንቸስኮና ቅዱስ ዶመኒኮስ በቅዱስ ወንጌል ተሐድሶ ተመርተው ያኔ ለቤተ ክርስትያን እጅግ ያስፈልግዋት የነበሩ የሦስት ዘርፎች ተሐድሶ አካሄደዋል። ፍራንቸስካውያንና ዶመኒካውያን ከቤተ ክርስትያንና ስለተፈጥሮ ጥሩነት የምታስተምረው ትምህርት ጋር በመተባበር መርጠዋል። ቀናተኛ ሰባካያነ ወንጌል እንደመሆናቸው መጠን በተለይም ድኆች በሚኖርበት የከተማ አካባቢዎች ወንድሞቹ ለምእመናን ትምህርተ ሃይማኖት በማስተማርና መንፈሳዊ አመራር እየሰጡ ሰርተዋል፣ ብዙ ምእመናንም የማኅበሮቻቸው ተከታይ በመሆን የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ሦስተኛ ማኅበርና የቅዱስ ዶመኒኮስ ሦስተኛ ማኅበር አቋቍመዋል። ከቦታ ወደ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ለአጠቃላይ የቤተ ክርስትያን ተሓድሶና ለኅብረተሰቡ መንፈሳዊ መለወጥ ምክንያት በመሆን ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል። በዩኒቨርስቲዎች በመመላለስም መነኮሳቱ በባህሉ ስብከተ ወንጌል በማትኮር እምነትና አእምሮ እንደማይጋጩ በማስተማር ትልቁ የመሀከለና ክፍለዘመን ፍልስፍናንና ንባበ መለኮትን ያጠቃለለ ስኮላስቲክ ቲዮሎጂ የሚባለውን መሠረቱ። የእነዚህ ቅዱሳን የቅድስና አብነትና በወንጌል የተመራ የአንዋንዋር ዘዴ የወንጌል ምስክሮች እንድንሆን ዘንድና ዓለምን ወደ ክርስቶስና ወደ ቤተክርስትያን ለመሳብ በምናደርገው ጥረት ይርዳን።”








All the contents on this site are copyrighted ©.