2010-01-13 15:09:03

ካኅናት፦ ጸላያን እና አማኞች


ኡኒታልሲ በመባል የሚጠራው ህሙማንን ወደ ሉድር ማርያም እና ወደ ተለያዩ ዓለም አቀፍ ቅዱሳት ሥፍራ መንፈሳዊ ንግደት የሚያጓጉዘው ማኅበር ባካሄደው ጉባኤ ንግግር ያሰሙት የኢጣሊያ የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት RealAudioMP3 ሊቀ መንበር በመሆን ያገለገሉ እና የሮማ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ኅይነት የነበሩ ብፁዕ ካርዲናል ካሚሎ ርዊኒ ይላሉ፣ በዘመናች የሚታየው እምነትን ችላ የማለት፣ አለ ማመን እና ማመን ያው ነው፣ የጋራ እሰይታ የሚባል የለም እያንዳንዱ በግሉ የሚለው ባህል ለጥሪ መጓደል ከሆኑት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ መሆኑ በመግለጥ፣ ማንም አማኝ ይሁን ካህን ጸላይ እና በእምነት ብርቱ መሆን ይገግባዋል ካሉ በኋላ፣ ካህን በቲዮሎጊያ እና በተለያዩ ባህሎች ጭምር የተሟላ ሕንጸት ያገኘ በጥበብ የተካነ መሆን እንደሚገባው እና የሃይማኖት ሰው ብቻ ሳይሆን የእምነት ሰው መሆን አለበት እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ክኅነት ጸጋ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ ነው። ስለዚህ እያንዳንዱ ካህን በሚስጢረ ክህነት በተቀበለው ጸጋ አማካኝነት ከቤተ ክርስትያን ከሓዋርያት ተከታዮች ጋር ኅብረት ያለው ነው ሲሉ፣ የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ክሮቻታ በበኩላቸውም ካህን እያንዳንዱ ምእመን ከክርስቶስ ጋር እንዲገናኝ የሚሸኝ፣ በግል እምነት የጸና ይኸንን እምነት በማኅበር የሚገልጥ፣ ከክርስቶስ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ያለው ለቤተ ክርስትያን እና በቤተ ክርስትያን የታመነ ቤተ ክርስትያን የሚያፈቅር እና በርሷ ላይ የሚያምን መሆን አለበት እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.