2010-01-13 15:07:44

ኤውሮጳ፣ ጸረ ድኽነት ዓመት


ዘንድሮ በጸረ ድኽነት ዓላማ የኤውሮጳ አገሮች አብረው በመተባበር እና የዚህ ዓላማ የማስፈጸሚያ ውሳኔ እግርብ ላይ እንዲያውሉ በመተባበር የሚቀሰቀሱበት ዓመት መሆኑ ሲገለጥ። ዓላማው ምክንያት በማድረግም የኤውሮጳ RealAudioMP3 ብፁዓን ጳጳሳት ድኽነት ለማስወገድ ጸረ ድኽነት ውሳኔ ለማረጋገጥ የቃል ብቻ ሳይሆን የተግባር ምልከቶች ማረጋገጥ ወሳኝ ነው በማለት፣ እ.ኤ.አ. የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. የመላ ኤውሮጳ የጸረ ድኽነት ዕለት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሮማ የሚገኘው በካሪታስ የሚጠራው ለድኾች ድጋፍ መስጫ እና መጠለያ ማእከል በመጎብኘት እዛው በማኅበሩ ከሚደገፉ ጋር አብረው የምሳ ግብዣ እንደሚቋደሱ ሲነገር፣ የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት በዚያች ዕለት መንግሥታት ማኅበሰብ እና እያንዳንዱ ዜጋ ጸረ ድኽነት ዓላማ እግብር ላይ ያውል ዘንድ በኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት የኅብረት ድርገት ሊቀ መንበር የሮተርዳም ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አድርያኖ ቫን ሉይን እና በካሪታስ ለሚጠራው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር በኤውሮጳ ተጠሪ ኣባ ኤርንይ ጊለን በጋራ ጥሪ አቅርበዋል።

ድኽነት ለማስወገድ እና ድኾች ለመርዳት የቤተ ክርስትያን እና የማኅበረ ክርስትያን ተቀዳሚ ዓላማ መሆን እንዳለበት በማሳሰብ፣ ድኾችን ማፍቀር በእያንዳንዱ ድኻ ውስጥ ያለው ክርስቶስ ማፍቀር ማለት መሆኑ በተላለፈው ጥሪ አመልክተዋል።

የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ማሪያኖ ክሮቻታ የተላለፈው ጥሪ በማስተጋባት በኢጣሊያ እና በተለያዩ የኤውሮጳ ሰበካዎች ቁምስናዎች ጸረ ድኽነት ተጨባጭ ምልክት እንዲሚቀርብ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.