2010-01-13 15:04:54

ኢራቃውያን ማኅበረ ክርስትያን


በኢራቅ ሞሱል ከተማ ጸረ ክርስትያን እና አቢያተ ክርስትያን ያቀና ጥቃት ከተነሳሳ ይኸው ዓመታት እያስቆጠረ ሲሆን፣ ከትላትና በስትያን በሞሱል ከተማ ከዶመኒካውያን ገዳም አጠገብ የሚገኘው የአንድ የአታክልት እና RealAudioMP3 የጥራጥሬ መሸጫ ሱቅ ባለ ቤት 75 ዓመት እድሜ የነበራቸው ኢራቃዊ ክርስትያን ዜጋ መገደላቸው አንዲት የክልሉ ነዋሪ የሆነቸው ወጣት ተማሪ ክርስትያን እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓመት ታህሳስ 31 ቀን ከተጠለፈች ወዲህ እስካሁን ድረስ አለ መገኘትዋ እና ስለ ሁኔታዊ የሚገልጥ ዜና ጭምር አለመገኘቱ ሲታወቅ፣ ጠለፋ፣ ግድያ እና በእሳት የማጋየት ተግባር የተሸኘ ጸረ ማኅበረ ክርስትያን እና አቢያተ ክርስትያን ያቀናው ጥቃት እና አመጽ የኢራቅ ክርስትያን ማኅበረሰብ አገሩን ለቆ ለስደት እያዳረገው ነው። ስለ ጉዳይ በማስመልከትም በሞሱሊ የሶርያ ስርዓት ለምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ ኣቡነ ጆርጀስ ካስሙሳ በስልክ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በሞሱል የማኅበረ ክርስትያን እና የአቢያተ ክርስትያን ደህንነት ዋስትናን የሌለው፣ ብዙ አቢያተ ክርስትያን ተደብድበዋል ክርስትያን ምእመናን ተገድለዋል፣ እየተገደሉም ነው እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ብቻ አራት ክርስትያን ምእመናን ተገድለዋል፣ ክርስትያን ምእመናን በክልሉ ያለው ሁኔታ ለሕይወታቸው ምንም አይነት ዋስትና የሌለው በመሆኑ እንዲሁም ወደ አቢያተ ክርስትያን የሚወስዱ ዋና ዋና መንገዶች ለጸጥታ እና ደህንነት በሚል ውሳኔ በመዘጋታቸውም ምክንያት ምእመናን በበዓለ ልደት ወደ ቤተ ክርስትያን ከመሄድ ተቆጥበው አቢያተ ክርስትያን ባዶ መቅረታቸው ገልጠው፣ የክልል መስተዳድርም ሆነ ማእከላዊው መንግሥት የሕዝብ ጸጥታ እና ደህንነት ለማረጋገጥ እያቃተው ነው።

የክልሉ ክርስትያን ማኅበረሰብ በባግዳድ በሞሱል እና በባሶራ በመሳሰሉት ከተሞች ለሕልውናው አደገኛ በመሆኑ ምክንያትም ወደ ሌሎች የኢራቅ ከተሞች እና ከኢራቅ ውጭ ለመሰደድ እየተገደደ ነው፣ ቅዱስ አባታችን በተደጋጋሚ ካለ መታከት ለኢራቅ ሕዝብ ጸጥታ እና ደህንነት ለክስትያን ማኅበርሰብ ሕልውና ዋስትና ይኖረውም ዘንድ በይፋ ጥሪ በማቅረብ የሚያስተላልፉት አጽናኝ መልእክት ለኢራቅ ቤተ ክርስትያን አቢያ ተስፋ እና ለብቻዋ እንዳልሆነች የሚያረጋግጥም የሚደነቅ እና የሚመሰገንም መልእክት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.