2010-01-13 15:10:26

ኡጋንዳ፦ የሰው ልጅ ጥበቃ


ከትላትና በስትያን እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. በኡጋንዳ በአንዳንድ የሴራ ሃይማኖትች እና ጣኦት አምላኪዎች ማኅበርሰብ ሰዎች መስዋዕት አድርጎ የማቅረብ ተግባር እየተፈጸመ መሆኑና 10 ሰዎች ለሓሰት አማልክቶች መሰዋታቸው RealAudioMP3 ከናይሮቢ ማቲው ፍራስኪኒ ኮፊ ያጠናቀረው ሰነድ የጠቀሰው አቨኒረ የተሰየመው የኢጣሊያ የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዕለታዊ ጋዜጣ በማሳወቅ፣ የኡጋንዳ መንግሥት ይኸንን ጉዳይ የሚያጣራ አንድ ድርገት መመልመሉም ጋዜጣው ይጠቁማል።

ባለፈው ዓመት ለሞት የተዳረጉት 15 ሰዎች እና የታገቱት 200 ሰዎች ጉዳይ ይህ የኡጋንዳው መንግሥት የመለመለው ድርገት እያጣራ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ሕጻናት ለተለያዩ ክብር ሰራዥ እና ጸያፍ ተግባር ብሎም የሰውነት የውስጥ አካል ብልት ለሕገ ወጥ የቀዶ ጥገና ሕክምና ለማዋል እና ለሴራ ሃይማኖቶች ሰው መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ለሚፈጽሙት ግድያ እንዲያገለግሉ ተብሎ የሚፈጸመው ከቦታ ቦታ የማዘዋወሩ አሰቃቂው እና ኢሰብአዊ ተግባር ለመዋጋት የአገሪቱ የጸጥታ እና የደህንነት ኃይሎች በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት የጸጥታ እና የደህንነት አባላት አማካኝነት ልዩ ሥልጠና እያገኑ መሆናቸው ተገልጠዋል።

ሰው መሥዋዕት አድርጎ ደሙን ማፍሰስ የሃብት ምንጭ ነው የተባለው ጠንቋዮች እና ፈዋሾች ነን ባዮች የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ በተመለከተ በክልሉ ላንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ስለ ሕፃናት ጉዳይ ለሚከራከረው እና ለሚረዳው የግብረ ሰናይ ማኅበር አባል ኤለና ሎመሊ በማስታወቅ በቅርቡ የብዙ ሕፃናት አስከሬን መገኘቱ እና የሞቱበት ምክንያት ለማጣራት የተከናወነው ሕክምና እንደሚያረጋገጠውም እነዚህ የተገደሉት ሕፃናት አንዳንድ የውስጥ አካል ብልት ጎደሎ ሆነው መገኘታቸው ለማወቅ ሲቻል ከዚህ ውጤት በመነሳትም፣ እነዚህ ሕፃናት የሰው የውስጥ አካል ብልት ለንግድ የሚያቀርቡ የወንጀል ቡድኖች ሰለባ መሆናቸው መሆኑ ለመረዳት አያዳግትም ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.