2010-01-13 17:00:15

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት እና በቅድስት መንበር የተመደቡ አምባሳደሮች፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ዘወትር በአዲስ ዓመት መባቻ እንደሚያደርጉት ሁሉ በዚህ አዲስ ዓመት 2010 ዓመተ ምህረት እኤአ በቅድስት መንበር የተመደቡት አምባሳደሮች በቫቲካን ተቀብሎዋቸውል።

ከትናትና ወድያ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና በአምባሳደሮቹ መካከል ቫቲካን ውስጥ በሚገኘው ሐዋርያዊ አዳራሽ የዓመት ጅማሬ ግንኙነት መካሄዱ የሚታወስ ነው።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዚሁ ግንኙነት ለአምባሳደራቱ ሰፊ ንግግር ማድረጋቸውም አይዘነጋም ። ንግግሩ በሰው ክብር የሥነ ሕይወት እና አከባቢ ጥበቃ ትኩረት የሰጠ መኖሩ ይታወሳል።

ሰርሚንግ የተባለ የሰላም ጥበቃ የሚከታተል ተቋም መስራች ኤርነስቶ ኦሊቨሮ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቫቲካን ለተመደቡ የአንድ መቶ ሰባ ስምንት ሀገራት አምባሳደሮች ያደረጉትን ንግግር በማስመልከት አስተያየት ሰጥተዋል።

ኤርነስቶ ኦሊቨሮ እንደገለጹት ፡ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ንግግር በተለያዩ ዓለም አቀፍ ርእሰ ጉዳያች የተመለከተ መኖሩ ጠቁመው ፡ ንግግሩ በሥነ ሕይወት እና የአከባቢ ጥበቃ በበለጠ ያተክረ መኖሩ በማስገንዘብ ፡ የአከባቢ መራቁት ለሰው ልጅ አደጋ ላይ ልጥል እንደሚችል አከባቢ መጠበቅ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የሰው ሕይወት መጠበቅ ማለት መሆኑ ያማላከተ እንደሆነ ገልጠዋል።

ራስ ወዳድነት እና ሥነ ሕይወትን አለመጠበቅ ራሱ የኤኮኖሚ ቀውስ ከማስከትሉ ሌላ ለሰላም እንቅፋት ሰበብ እንደሚሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለአምባሳደሮቹ ጠቁመው ይሰው ልጅ ከስህተቱ እንዲማር ማሳሰባቸው መልካም መኖሩ ሰርሚንግ የተባለ ይሰላም ጉዳይ የሚከተተል ተቋም መስራች ኤርነስቶ ኦሊቨር ገልጠዋል።

አያይዘውም ቤተክርስትያን የሰብእውነት መምህር እና ምስክር እንደመሆንዋ መጠን በርዋ ለሁሉ ክፍት መሆኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለአምባሳደሮቹ በማረጋገጥ ከስዋ ጋር በቀጥታ ለመወያየት እንደሚቻል ማመለከታቸው መልካም መሆኑ እና በሳቸው አስተያየት ይህ የሁሉም ትኩረት ስበዋል ብለው እንደሚያስቡ አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ሀገራት በክርስትያኖች ላይ የሚፈጸመው ዓመጽ እና ማሳደድ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው አጽንኦ ሰጥተው መናገራቸው እንደተገነዘቡ ኤርነስቶ ኦሊቨር አስታውሰዋል።

በዓለም ዙርያ የሃይማኖት ነጻነት እንዲኖር ሃይማኖት የሥልጣን ማወጣጫ መሳርያ መሆን እንደማይገባ ይህም እንዲገታ ትኩረት ከሰጡት ዓቢይ ነጥብ አንዱ መሆኑ አያይዘው መናገራቸው ገልጸዋል።

የኤውሮጳ የክርስትና እሴቶች መታደግ ሲገባቸው በአንዳንድ ቦታዎች ይህ ሲጓደል ማየት ማንነት መርሳት ወይም መሰረዝ መምሰሉም ከፈጣሬ ኩሉ ዓለም መፈንቀቅ ያህል መሆኑ ቅድስነታቸው ማመልከታቸው ያስታውሱት ኤርነስቶ ኦሊቨር በአጠቃላይ ንግግሩ ግሩም መኖሩ ይናገራሉ።

በሰሜናዊ ኢጣልያ በፓዶቫ ዩኒቨርሲቲ የሀገራት አቀፍ ግንኙነት መምህር ፕሮፈሶር አንቶንዮ ፖፒስካ በበኩላቸው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቫቲካን ለተመደቡ አምባሳደሮች ያደረጉት ንግግር ፡ የሰው ልጅ ማእከል ያላደረገ የፖሊቲካ እና ኤኮኖሚ ሥርዓት ደካማ እና መስመር የሳተ መሆኑ የሚያመላክት ነበር ብለዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ባለፈው ቅርብ ግዜ የጻፉት Caritas in veritate ሐቅ በፍቅር ላይ ይገኛል በተሰኘ ሐዋርያዊ መልእኽት መልእክትም ከሁሉም በላይ የሰው ክብር እና ግርማ ቀዳምነት እንዲሰጠው አጽንኦት ሰጥቶ ማሳሰሰቡ እና እንደ ቅድመ ግዴታ ማቅረቡ አስታውሰው የቤተክርስትያን ትምህር መሆኑ አማንያን ኢ አማንያን ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች የሚመለከት እንደሆነ ፕሮፈሶሩ ገልጠዋል።

አያይዘው አፍሪቃ ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች ተወግደው አፍሪቃ ወደ እድገት እንድታመራ እንደሚሹ የመካከለኛው ምስራቅ የቆየ ውዝግብ የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የሰላም እጦት መፍትሔ እንዲገኝለት የክልሉ ክርስትያኖች ስቃይ እንዲያበቃ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ በቅድስት መንበር ለተመደቡ አምባሳደራት ያደረጉት ንግግር ወቅታዊ እና የሚደገፍ መሆኑ ፕሮፈሶር አንቶንዮ ፓፒስካ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.