2010-01-13 11:39:08

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ብፁዕ ካርዲናል ኤትቸገራይን ጐበኙ፡

 


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሮማ ውስጥ ወደ ሚገኘው ጀመሊ ሕክም ቤት በመሄድ ብፁዕ ካርዲናል ኤትቸገራይን መጐብኝታቸው የቫቲካን ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ኤቸገራይ ባለፈው የገና ዋዜማ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ከሌሎች ካርዲናላት እና ብፁዓን ጳጳሳት በቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል መስዋዕተ ቅዳሴ ለማሳረግ ወደ መንበረ ታቦት ባቀኑበት ግዜ አንድ ሱዛና ማዮሎ የተባሉ ጐልማሳ ሴት በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ላይ በመጫን እንዲወድቁ ሰበብ በሆኑበት ግዜ አጠገባቸው የነበሩ ብጹዕ ካርዲናል ኤትቸገራይ ወድቀው በጭናቸው ላይ በደረሰባቸው ጉዳት ወደ ጀመሊ ሕክምና ቤት መወሰዳቸው እና ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው የሚታወስ ነው ።

ቃል አቀባዩ በሰጡት መግለጫ መሠረት ፡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ጀመሊ ሕክምና ቤት እንደ ደረሱ ፡ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ዳይረክተር ፕሮፈሶር ኦራንጊ የሕክምና ቤቱ ዋና ሐላፊ ፕሮፈሶር ካታናንቲ እና የሕክምና ቤቱ ባለ ሙያዎች ሙቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከብፁዕ ካርዲናል ሮጀር ኤትቸገራይ ለግማሽ ሰዓት መቆየታቸው እና የጠናቸው ሁኔታ በቅርብ መረዳታቸው የቫቲካን ቃል አቀባዩ ለጥቀው አመልክተዋል።

የቫቲካን ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ እንደገለጹት ብፁዕ ካርዲናል ኤትቸገራይ የተደረገላቸው ቀዶ ጠገና እና ሕክምና በመሳካቱ በተያዝነው ሳምንት አጋማሽ ወይም መጨረሻ ሕክምና ቤቱ ለቀው ይወጣሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.