2010-01-11 14:07:18

የቶጎ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ውሳኔ


ዘንድሮ መአንጎላ በሚካሄደው የአፈሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ለመሳተፍ አንጎላ የገባው የቶጎ ብሔራዊው የእግር ኳስ ምርጥ ቡድን በካቢንዳ ክልል ከአማጽያን በደረሰብት ጥቃት ሳቢያ ሦስት ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው RealAudioMP3 የሚታወስ ሲሆን፣ ቶጎ በዚህ ዘንድሮ በሚካሄደው የእፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር እንደማትሳተፍ ተሰላፊዎች እና በጠቅላላ የቶጎ ብሔራዊው የእግር ኳስ ምርጥ ቡድን ወደ አገሩ እንዲመለስ የቶጎ መንግሥት ያስተላለፈው ውሳኔ ቡድኑ እንደሚያክበረው የቡድኑ ተሰላፊዎች የሰጡት መግለጫ የጠቀሰው አርኤምሲ በመባል የሚጠራው የፈረንሳይ ረድዮ አስታወቀ።

ስለ ደረሰው ጥቃት በማስመልከት የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ የትርፍ ጊዜ የመስህቦ ኣና የስፖትር ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚመለከተው ጽ/ቤት ተጠሪ ኣባ ማሪዮ ሉሰክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በቶጎ ብሔራዊው የእግር ኳስ ምርጥ ቡድን ላይ የተጣለው ጥቃት የአፍሪቃ ማህበራዊ እና ፖሊቲካዊ ጉዳይ ምን እንደሚመስል የሚያንጸባርቅ ነው። ቅዱስ አባታችን ባለፈው ዓመት እዚህ በቫቲካን በተካሄደው ሁለተኛው ይፋዊው የአፍሪቃ ሲኖዶስ ወቅት ባሰሙት ንግግር፣ የሲኖዶሱ ርእስ ሰላም ፍትሕ እና እርቅ የሚሉትን ነጥቦች በጥልቀት በመመልከት የሰጡት መሠረታዊ ሀሳብ በዚህች ክፍለ ዓለም የሚከናወን ማንኛው ባህላዊ ጉዳይ እርቅ እና ሰላም ወንድማማችነት የተለያዩ ባህሎች እና ጎሳዎች የሚያገናኝ አጋጣሚ መሆን እንደሚገባው የሚያብራራ ነው። ባህላውያን አጋጣሚዎች የተለያዩ አማጽያን ኃይሎች ተገን በማድረግ ሊጠቀሙበት የተነሳሱ ነው የሚመስለው፣ እጅግ የሚያስፈራውም በደሙብ አፍሪቃ ሊካሄድ ተወስኖ ላለው እና ሊጀመር ጥቂት ወራት ለቀረው ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር እንዳያሰናክልም ያሰጋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.